ኢህአዴግና የተዳፈነው ፍም

ደረጀ ሀብተወልድ ከሆላንድ

የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ በኢህአዴግ ውስጥ የሥልጣን ሽኩቻ እና ሊፈነዳ የደረሰ ቂም እንዳለ በስፋት ይወራል። እርግጥ ነው፤ ባለፉት ዓመታት በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በተለይም በህወሓት እና በብአዴን መካከል ተዳፍነው የቆዩት የቂም እሳቶች በገሀድ የሚነድዱበት ጊዜ ላይ የደረስን ይመስላል። ስፍር ቁጥር ከሌላቸው የነ አቶ በረከት እና የህወሓቶች ቁርሾዎች መካከል ለዛሬ አንዱን እንመልከት።