ህዝባቸውን ለመመገብ አስጊ ሁኔታ ላይ ያሉ ሀገራት

ማፕልክሮፍት ያወጣው ደረጃ በምግብ እጥረት ሳቢያ ህዝባቸውን መመገብ የማይችሉ ካላቸው ውስጥ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው።

ማፕልክሮፍት የተሰኘው የብሪታንያ የአየር ንብረት ተመራማሪ ድርጅት ፤ ለተባበሩት መንግሥታት የምግብ ድርጅት ፤ ስለምግብ ዋስትና ባደረገው ጥናት ፤ ህዝባቸውን በሚገባ መመገብ የሚችሉትን አገሮችና በምግብ እጥረት ለአደጋ ሊጋለጡ የሚችሉትን ዝርዝር በማውጣት አስታውቋል። በጥናቱ መሠረት ፤ የሰሜን አሜሪካ አገሮች፤ ከአውሮፓም ፤ ፊንላንድ፤ እስዊድን፣ ኖርዌይና ደንማርክ ላቅ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። ከዚህ አንጻር፤ በሰላም ማጣት የምትታመሰው አፍጋኒስታንና በተለይ 9 የአፍሪቃ አገሮች፤ በከፍተኛ የምግብ እጥረት ሳቢያ፤ ህዝባቸውን ለመመገብ እንደሚሳናቸውና አሥጊ ደረጃም ላይ እንደሚገኙ ሠንጠረዡ ያስረዳል። ያዳምጡ፤