ወቅታዊ ጉዳይን በሚመለከት ከኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን መ/ፓትርያርክ ጠ/ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተሰጠ መግለጫ
(ደጀ ሰላም፤
መስከረም 11/2004 ዓ.ም፤ ሰምቴፕር 21/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ “ወቅታዊ ጉዳዮችን” አስመልክቶ ሁለት
መግለጫዎችን እንዳወጣ ታወቀ። በመምሪያ ኃላፊው በአቶ እስክንድር ገ/ክርስቶስ ኃ/ማርያም ስም ይፋ የተደረጉት ሁለቱ መግለጫዎች
በአገሪቱ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ም/ጠ/ሚኒስትር ሹመት እና ተያያዥ ጉዳዮች እንዲሁም በስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ እና ተያያዥ
ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው።

በተለይም በአዲስ ፓትርያርክ ምርጫ እና ተያያዝ ጉዳዮችን የሚያትተው መግለጫ
“የሽግግር ወቅት ሂደቱ በሰላማዊ መንገድ እንዳይራመድ በቤተ
ክርስቲያኒቱ ውስጥና ዙሪያ የተሸሸጉ አንዳንድ ጥቅመኞችና የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰላማዊ አካሄድ የማይዋጥላቸው ግለሰቦች” ያላቸው “ከሚነዙት መሠረተ ቢስ አሉባልታ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል”።
አክሎም “‹የስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫና መሰል
ጉዳዮች በጥቅምቱ ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ይወሰናል” ብሏል። በአገሪቱ ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካ ሒደትና የአዲስ ጠ/ሚኒስትር መሾምን
በሚመለከት የሚያትተው ሌላውም መግለጫ “ቤተ ክርስቲያናችን
ዛሬም እንደ ጥንቱ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ ለልማትና ለሰላም ቅድሚያ ሰጥታ ትንቀሳቀሳለች” ብሏል።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን