ተሸናፊው ሶፊያን አህመድ ነበር
ተስፋዬ ገብረአብ
የኢህአዴግ ምክርቤት ጉባኤ ተጠናቆአል። ምክር ቤቱ ሃይለማርያምና ደመቀን ዋና እና ምክትል አድርጎ መርጦአል። በዚህ ምርጫ አነጋጋሪ የሆነው፣ ከምርጫው በፊት፣ “ታጋይ የነበረ ለምርጫ አይቀርብም” በሚል ማሳሰቢያ ከበረሃ የገቡ ታጋዮች ሁሉ ራሳቸውን ከምርጫ ማግለላቸው አንዱ ነበር። በጥቆማው ወቅት ከህወሃት እጩ ሆኖ ለውድድር የቀረበ አለመኖሩ ሌላው አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖአል። ሶስት ሰዎች ተጠቆሙና ሁለቱ ተመረጡ።