የሁለት ወራት መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት መኖሩን አይኤምኤፍ አስታወቀ

በአስራት ሥዩም

በአገሪቱ ያለው የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሪ ከሳምንታት ያልዘለለ ነው እየተባለ ወሬ ቢናፈስም፣ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ኢትዮጵያ ለሁለት ወራት የሚበቃ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዳላት አስታወቀ፡፡