በሐሰት ወሬ ሕዝብን ለአመፅ አነሳሳ የተባለ ግለሰብ በአንድ ዓመት እስራት ተቀጣ

በሊያ ተረፈ

የፌዴራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አምስተኛ የወንጀል ችሎት፣ በመንግሥት ላይ ጥላቻን ለማስፋፋት በማሰብ ሕዝብን በሐሰት ወሬ አነሳስቷል የተባለውን ግለሰብ፣ በአንድ ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መስከረም 3 ቀን 2005 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ውሳኔ ሰጠ፡፡