የኢህአዴግ ምክር ቤት መሪዎቹን መረጠ

አቶ ደሳለኝ ኃይለምሪያም ሊቀመንበር ሲሆኑ በምክትልነት አቶ ደመቀ መኮንን ተመርጠዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም 5 ቀን 2005 .. September 13, 2012)፦ ለበርካታ ወራት ቁርጡ ባልታወቀ የአመራር ክፍተት ሲታመስ ነበረው ህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት ከ21 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አመራሩን የመረጠ ሲሆን በዋና ሊቀመንበርነት አቶ ደሳለኝ ኃይለማሪያምን እና አቶ ደመቀ መኮነንን በዋናና ምክትል ሊቀመንበርነት ሰየመ።