የስዊድን ጋዜጠኞችን ጨምሮ 1923 እስረኞች ይቅርታ ተደረገላቸው

–    ስዊድናዊያኑ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ የተወሰነው በሐምሌ ወር ነበር

በታምሩ ጽጌ

በፓርላማ ሽብርተኝነቱ የተረጋገጠውን የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ)ን ዓላማ በመደገፍና የአገር ሉዓላዊነትን በመድፈር ድንበር መሻገራቸው፣ በሰነድና በሰዎች ምስክሮች ተረጋግጦባቸው 11 ዓመታት እንዲታሰሩ የተፈረደባቸው ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች ጨምሮ 1923 ታራሚዎች ዛሬ ከማረሚያ ቤት ይለቀቃሉ፡፡