ከቀረጥ ነፃ በገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ የተላለፈው ውሳኔ ተቃውሞ ገጠመው

በውድነህ ዘነበ

–    በባለሥልጣኑ ውሳኔ የተበሳጨው የአስጎብኚ ድርጅቶች ማኅበር  ስብሰባ ጠርቷል

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከቀረጥ ነፃ የገቡ ተሽከርካሪዎችን በሚመለከት ያሳለፈው ውሳኔ ከጉዞ ወኪሎችና አስጎብኚ ድርጅቶች ማኅበር ተቃውሞ ገጠመው፡፡