የሲንጋፖር ንግድ ልዑካን ለመጀመርያ ጊዜ በአዲስ አበባ ጉብኝት እያደረጉ ነው

በብርሃኑ ፈቃደ

ሩቅ ምሥራቃዊቷ ሲንጋፖር ያላት ሕዝብ አምስት ሚሊዮን ከመሆኑም በላይ አነስተኛ የደሴት አገር ብትሆንም፣ ከ35 ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ከሦስተኛው ዓለም ተርታ ወጥታ ወደ ኢንዱስትሪያው ያደጉ አገሮች ሰልፍ ውስጥ ራሷን ያስተካከለች ትንሽ አገር ናት፡፡