የአክቲቪስትና አርቲስት ታማኝ የአውስትራሊያ ቆይታ ጠቅላላ ሪፖርት
ላለፉት 8 ዓመታት አገራዊ ፋይዳ ያላቸውንና ለህዝባችን ሁለንተናዊ ነጻነት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ሲንቀሳቀስ የቆየው የሜልበርን ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን ባደረገለት ግብዣ በ 12/08/12 አውስትራሊያ የገባው ተወዳጁና እውቁ የጥበብ ሰው አርቲስት ታማኝ በየነ በአውስትራሊያ 5 የተለያዩ ከተሞች ማለትም በሜልበርን ፤ በሲድኒ፤ በአድላይድ፤ በብሪዝበንና በፐርዝ በተከናወኑ የኢሳት ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ላይ በመገኘት ከ 115 ሺህ በላይ ዶላር ማሰባሰብ ችሏል።