በሐዋሳ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲታከሙ አስመስለው የተነሱ ፎቶዎችን ሲሸጡ የተገኙ በፖሊስ ተያዙ

በአስፋው ብርሃኑ፣ ልዩ ዘጋቢ ከሐዋሳ

በሐዋሳ ከተማ የጠቅላይ ሚኒስትር  መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ሕይወት ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በርካታ ፎቶግራፎች ሲሸጡ የሰነበቱ ሲሆን፣ በሕክምና ላይ እያሉ አስመስለው የተነሱ ፎቶግራፎችን ሲሸጡ የተገኙ ግለሰቦች ደግሞ በፖሊስ ተይዘዋል፡፡