የጎዳና ልጆች ለቅሶ (ሄኖክ የሽጥላ)
በዚች ግጥም ልግባባችሁ…
“እንባ እንደ ጅረት ፈሰሰ
ደረት ኢንደ አፈር ፈረሰ
ምድረ ጭርንቁስ ድሃ
ተቃቀፈና አነባ
ግና ያለፈ እናዳላረፈ አረፈ
አየ አየና አለፈ”
አለ ገጣሚው…እውነት ነው ዛሬ ሃገራችን ደረት እንዳፈር ፈርሶዋል…እነባ እንደጅረት ፈሶዋል የዘመናት በደሉን የሚገልጽበት ነጻ መድረክ ተከፈተለት…”አያ ጅቦም አመካኝቶ በልቶዋል”:: ኢትዮጵያዊነት የሚያሳየን ብዙ ድራማዎችም አሉ…ይቀጥሉማል:: ለውሾቻቸው የታሸገ ምግብ መግዛት ከጀመሩት የቦሌ የሃያት እና የገብርኤል ሰፈር ሃብታሞች ላስኪት ወጥረው የቆሻሻ ገንዳ ግርግዳ አድርገው ከሚኖሩት ያገሬ የጎዳና ተዳዳሪዎች ሃዘናቸው እንዲገልጹ ተደርጎዋል እየገለጹም ነው:: የዛሬ ጸሁፌም የሚያተኩረው ሁለተኞቹ ላይ ነው።
አንባቢያን ኢንደምታውቁት middle class ወይም በኔ ድፍየና መሃል ሰፋሪ ስለተባሉት የህብረተሰብ ክፍሎች ጊዜ ካገኘሁ እመለስበታለሁ:: አሁን ግን “ሃሳቡ እንዲገባችሁ” እኔም እንደ አቤ ቶኪቻው በአዲስ መስመር እጀምራለሁ።
ያዲስ አበባ ጎዳና ተዳዳሪዎች በጠቅላይ ሚንስትሩ መሞት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ:: ሃዘናቸው ያተኮረባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች እንደሚከተለው ይቀርባል።
እኛ ባራት ኪሎና በአካባቢዋ የምንኖር የጎዳና ተዳዳሪዎች በጠቅላይ ሚንስትራችን መሞት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን ስንገልጥ በብርድ የተሰነጠቀ በጸሃይ የጠቆረ በቅማል ወንፊት የሆነ ፊታችንን ኢንደምታዩት በሃዘናቸው ከከፊል ደመናማነት ወደ ከል ሰማይነት እንደተቀየረ ለማስገንዘብም እየሞከርን ነው:: ተቅላይ ሚንስትራችን በህይወት ባሉ ጊዜ…የሰው ልጅ በእውነትም ሊለምደው ይችላል የማይባለውን ነገር ያስለምዱን ታላቅ መሪ ናቸው።
ከበርሃ በቀሰሙት ልምዳቸው ያለምግብ ለሳምንታት ኢንዴት መኖር እንደሚቻል ብቻ ሳይሆን ባንድ ልብስ ላይውም በበከተና በተባይ በተወረረ ብጫቂ ጨርቅ ራስን ንቆ እንዴት መኖር እንደሚቻል አስተምረውናል:: ጠቅላይ ሚንስትራችን በህየውት በነበሩ ጊዜ “ክርስቶስ በሓጣንና በጻድቃን ላይ ለመፍረድ በድጋሚ ወደዚች ምድር ይመጣል” የሚለውን አባባል ” በቀን ሶስቴ ትበላላችሁ” በሚለው ተክተን እንድናምን ያደረጉን ታላቅ ሰው ነበሩ።
ጥቅላይ ሚንስትራችንን በይበልጥም ክረምት ሲመጣ “አይዞአችሁ በሃምሌ ዝናብ ተደብደቡ ..ታዛ መጠለያ አይኑራችሁ…ፌደራል ፖሊስም ሌባ እያለ ይደብድባችሁ” ብለው የመከሩንን አንረሳውም:: ጠቅላይ ሚንስትራችን በህይወት በነበሩ ጊዜ አርቆ አሳቢነታቸውን ካሳዩበት መንገዶች ወስጥ እኛ የጎዳና ተዳዳሪዎች እየበዛን በመጣንበት ሰአት “አይዞአችሁ አዲስ ቀለበት መንገድ እሰራላሁ ” ባሉት መሰረት ቃላቸውን ሳያጥፉ ከሚቆረቁረውና ከገረጋንቲው ጎዳና አውጥተውን ፎቅና ምድር የቀለበት መንገድ የሰሩልንን በፍጹም ከህሊናችን የሚጠፋ አይደለም።
ከኛ ከጎዳና ታዳዳሪዎችም መሃል ተቅላይ ሚኒስትሩን በሙሉ አይኖቻችን ያየናቸው ብዙ ነን። ይሄ ደሞ አብዛኛው ኢትይኦጵያዊ በተኛበት ሰአት ለሽርሽር ወደ ውጭ በሚወጡበት ጊዜ ሲሆን…ምን ያህል ንቁና የማይተኙ ሰው መሆናቸው ደሞ ከኛ ጋ በፍጹም ያመሳስላቸዋል:: በይበልጥ አንዳንዴ…ተቅላይ ሚንስተር መለስ ዜናዊ ሰውነታችን ላይ ትልቅ ቅማል ሲያዩ “ይሄ ቅማል እኔ በርሃ እያለሁ አብሮኝ የነበረውን ይመስላል ምናልባትም የኔ ቅማል ለናንተ ቅማል ቅድመ አያቱ ሳይሆን አይቀርም” እያሉ አንድ መሆናችንን ይነግሩናል።
ባለፈ ጊዜ ለሚሊኒየም ሸራተን አዲስ ዝግጅት በነበረ ጊዜ…ከሰው የተረፈው ከሚደፋ ከሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ጋ በመነጋገር እኛ እንድንበላው ያደረጉት በፍጹም አይረሳንም:: አልፎም ተርፎም በሃገር ውስጥም ይሁን ወውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሉጢዎች በየመኖሪያ ቤቶቻችን እያስገደዱ እንዲደፍሩን …ሃገራችንን ሃገር ሳይሆን ቡና ቤት ኢንድትሆን ስላደረጉአት ሃዘናችን ጥልቅ ነው:: ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ሃዘናችንን ያበረታብን “የጎዳና ተዳዳሪዎች እኩልነት” የሚለውን ረቂቅ አዋጅ ከመጽደቁ በፊት እንድንመለከተው ሰጥተውን ማስተካከያው ቸርሰን ለመመለስ በምንዘጋጅበት ሰአት ማለፋቸው ሃዘናችንን አበርክቶብናል። ለቂቅ አዋጁ እንዲ ይል ነበር….
የጎዳና ተዳዳሪዎች የእኩልነት አዋጅ የሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ እንደሚያሳየው በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ህዝብ ቤት ውስጥ ከመኖር ወደ ጎዳና መውጣትን መርጦዋል…ነገሩ ይበል የሚያስብል ነው:: ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ በሚቀጥሉት 10 አመታት ውስጥ 40 ከ 100 የሚሆነው የሃገራችን ህዝብ ወደ ጎዳና ይወጣል ተብሎ ይገመታል የተቀረው 60% ደግሞ በጎዳና አቁዋርጦ ወደ ሌሎች ሃገርኦች ይሄዳል…ስለዚህ “አዎ ስለዚህ ይላል አዋጁ” …ስለዚህ ከዚህ ቀደም ያልነበረ አሁን ግን የሚያስፈልገንን ይሄን አዋጅ ስናጸድቅ የጎዳና ተዳዳሪዎች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጁን ከተመለከት በሁዋላ በድምጽ ብልጫ ያጸድቀዋል።
አዋጅ… ከዛሬ ከ ጥቅምት ገለመኔ ጀምሮ ሁሉም የጎዳና ተዳዳሪዎች በመረጡት ጎዳና ላይ የመኖር መብታቸው በህግ የተጠበቀ ነው:: ማንኛውም የጎዳና ተዳዳሪ በሚገባው ቁዋንቁ መነጋገር ይችላል። ከንዚህም ውስጥ የልመና ቁዋንቁዋ የጥግረራ ቁውንቁዋ ያራዳ ቁዋንቁዋ ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ:: ማልቀስ ብሄራዊ ቁዋንቁዋቸው እንዲሆን ወስነናል። ምክር ቤት ቀደምት የጎዳና ተዳዳሪዎችና አድሃሪ የቆሎ ተማሪዎችን ለመቆጣተር ሲል በጎዳና ተዳዳሪዎች መሃከል ቅኔ የሚናገር…ወደ በቱ ተመልሶ የሚገባ እና ወዘተን በ 15 አመት ጽኑ እስራት የቀጣል። እስራቱም የሚፈጸመው መንገድ ፈጽሞ ካልገባባቸው አካባቢዎች ሄዶ አዲስ ኑሮ እንዲጀምሩ በማድረግ ይሆናል:: ይላል!
በመጨረሻም የጠቅላይ ሚኒስትሩ መሞት በተመለከተ የተሰማንን ልባዊ ኢየገለጥን እኛ የጎዳና ተዳዳሪዎች ብቻዎትን እንዳማይተኙ አብረንዎ ከበን እሳት እየሞቅን እንደምንተኛ ቃል ኢንገባሎታለን። በመጨረሻም በቅርቡ እኛን ለተቀላቀሉት ጠቅላይ ሚንስትራችን ቤተሰቦች መጽናናቱን እየተመኘን…የተቅላይ ሚንስትራችንን መሞት ተከትሎ በሚደረገው ሃገራዊ የድንኩዋን ሰበራ ላይ እየተሳተፉ ያሉትን በጎዳናና በቤት መሃከል የሚኖሩ ወገኖቻችንን..እንኩዋን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለ መለስ ዜናዊ በአለ ሞት አደረሳችሁ አደረሰን እያልን… እኛም በ-አምስት አመት መርሃ ግብራቸው ውስጥ ካካተቱት የዘኬ ለቀማችን እንሄዳለን:: ድል ለችግርና ረሃብ! ያዲሳባ ጎዳና ተዳዳሪዎች…ነሃሴ ምንትስ ሺ አርት መቶ አራት!