ሀዘን ለመግለጽ የተሰበሰቡ አርቲስቶች የእዝን መዋጮ ተጠየቁ

ሰራዊት ፍቅሬና እቁባይ በርሄ ሚና ተጫውተዋል

ልዩ ሪፓርታዥ (ከአዲስ አበባ)

Ethiopia Zare (ማክሰኞ  ነሐሴ 22 ቀን 2004 .. August 28, 2012)፦ የአቶ መለስ ሞትን ተከትሎ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ዜጎች ሀዘናቸውን በአደባባይ ወጥተው እንዲገልጹ በድርጅታዊ አሰራር እየተገደዱ መሆኑ ሲታወቅ በየመስሪያ ቤቱና በየዩኒቨርሲቲዎቹ ያሉ ሰራተኞችና ተማሪዎች ጥቁር ለብሰው በተወሰነ ሰዓት እንዲሰባሰቡ የታዘዙባቸው ደብዳቤዎች ለይፋ እይታ በቅተዋል። በተመሳሳይ መልኩ ለገዥው መንግስት ሁነኛ አገልጋይ በሆኑት በሰራዊት ፍቅሬ እና በእቁባየይ በርኸ  አስተባባሪነት የተሰባሰቡ አርቲስቶች የእዝን ገንዘብ ቃል እንዲገቡ መደረጉን በስፍራው የተገኘው የኢትዮጵያ ዛሬ ተባባሪ ሪፖርተር አመልክቷል።