የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥርዐተ ቀብር በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 21/2004
ዓ.ም፤ ኦገስት 27/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተሰማው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዐተ ቀብር፣ እሑድ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2004 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገለጸ፡፡
ዓ.ም፤ ኦገስት 27/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተሰማው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዐተ ቀብር፣ እሑድ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2004 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገለጸ፡፡
የቀብር አስፈጻሚው ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት በፌዴሬሽን ም/ቤት በሰጠው መግለጫ ነሐሴ 24 እና 25 ቀን 2004 ዓ.ም፣ ከቀኑ 11፡00 – ምሽት 1፡00 ድረስ በመስቀል አደባባይ በሚካሄደው መርሐ ግብር የተለያዩ አብያተ እምነት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ሐዘናቸውን የሚገልጹበት ሥነ ሥርዐት መዘጋጀቱን የቀብር አስፈጻሚው ኮሚቴ አባላት ለዜና ሰዎች የሰጡት መረጃ አመልክቷል፡፡
እሑድ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2004 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚፈጸመው ሥርዐተ ቀብርም እስከ አሁን ድረስ ከ20 ያላነሱ የአፍሪካ አገራት መሪዎች እንደሚገኙ ማረጋገጡን የቀብር አስፈጻሚው ኮሚቴ ገልጧል፡፡ በብሔራዊ ቤተ
መንግሥት እየከተከናወነ በሚገኘው የሐዘን መግለጽ ሥነ ሥርዐት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተለያዩ ቀናት እየተገኙ ጸሎት በማድረግ አጽናንተዋል፡፡
መንግሥት እየከተከናወነ በሚገኘው የሐዘን መግለጽ ሥነ ሥርዐት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተለያዩ ቀናት እየተገኙ ጸሎት በማድረግ አጽናንተዋል፡፡
ተጨማሪ ዜናዎችን ይከታተሉ፤
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡