በፍጥነት፤በከፍተኛና፤ በጥንካሬ። ዳኮታ የጥናት ማእከል።
በያዝነው ሀምሌ ወር በዩኬ ታላቁ ያኦሎምቢክ ውድድር ተደርጎ ነበር። የበአሉ ሙቀት በያለንበት ሁላችንንም ሲሰማን ቆይቷል። የኛ ጀግኖችም መዳሊያ አግኝተዋል። በዚህ አመት የተለመደውን አቀባበል ህዘብ እንዲያደርግላቸው አልተደረገም።
“Citius,Altius, Fortius” Latin for “faster, Higher, stronger. የላቲን ቃላት ሲሆኑ በፍጥነት፤ በከፍታኛና ፤ በጥንካሬ ለማለት ነው።
ወደ ኦሎንቢኩ እንመለስና በፍጥነት በከፍተኛ፤ በጥንካሬ የሚሉት ቃላት አትሌቶች ያሸናፊነትን መንፈስ ለማላበስና ለማበረታት ቃላቶቹ በዝተው የተሰሙበት ወር ነበር። የኛ ውድድርና ማሸነፍ በኦሎንቢኩ ብቻ አልሆነም። አሸናፊ ለመሆን በፍጥነት፤ በከፍተኛና፤ በጥንካሬ ልንሰራቸው የሚገቡ ብዙ ጊዜው ግድ የሚላቸው ጉዳዮች አሉብን።
አንደኛውና ዋንኛው የትብብር ጉዳይ ነው። ሁሉን አቀፍ ትብብር በትግሉ ባህሪ ምክንያት ወሳኝ ስለሆነና በሽግግሩ ወቅት ለምንጋፈጣቸው ለበዙት ችግሮች አሌ የማይባሉ መፍትሄነቱ ምክንያት ዜጎች ጥያቄያችን ካደረግነው ቆይቷል። የድል ጎዳናን የሚጠርግ፤ ከዳር እስከዳር በዜጎች ሁሉ ሊሰማ የሚችል ትብብር ድሮ ገና ሊደረግ የተገባም የሚቻልም ነበር። ይህ ታላቅ ጉዳይ እዚህም እዛም ትናንሽና በጭራሽ አሸናፊ ሊያደርጉን በማይችሉ ሰፈራ በመሰሉ ብዙ ስብስቦችን በመፍጠር ሊዳፈን የደረሰበት ሁኔታ ላይ ተደርሶ ነበር።
ጥሩነቱ የዚህ አይነቱን ትብብር አስፈላጊነት የጊዜው ያገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ጠንካራ የሆነ የህዘብ ግፊት ተጨምሮበት በአዲስ መልክ ተግባራዊ ልናደርገው የሚገባ አድርጎታል። በመጨረሻ እውን የሚሆንም ይመስላል። አሁንም የምንለምነው በፍጥነት፤ በከፍተኛና ጠንካራ በሆነ ሁኔታ እንዲተገበር ነው።
አስራ አንዱ አሉ የሚባሉ ድርጅቶች ትብብር ለመመስረት የተስማሙበትን መግለጫ አይተን እጅጉን ነው የተደሰትነው። ስንጎተጉት የነበረውም የህንን አይነቱን ትብብር ነበር። ይህ ብዙ ድርጅቶችን ያቀፈ የበዙትን የማህበረሰብ ክፍሎች ሊያንቀሳቅስ የሚችል ታላቅ የትብብር ጅማሮ ነው። በጠንካራ ሁኔታ ትብብሩን ማቆም ከቻሉ ሁሉን አቀፍ ትብብር ሊሰኝ ይችላል። የልተካተቱ ድርጆቶች እንዳሉ እናውቃለን። ትብብሩን የተሻለ ውጤታማና ሙሉ ለማድረግ መካተት የግድ አለባቸው። ለመካተታቸው የበዛው ህላፊነትም አሁን በጋራ ለመስራት የተስማሙት ድርጅቶች ነው የሚል እምነት አለን። ቆማችሁ ግን አትጠብቋቸው ትግሉ እየተካሄደ።
1- ኢሀፓ። ይካተታሉ የሚል ጠንካራ እምነት ነው ያለን። ትብብሩ ውስጥ ድርሻ በማድረጋችሁ ትብብሩን ጠንካራና ተሰሚ እንዲሆን በማድረግ ከሚኖራችሁ ጠቀሜታ በላይ ለሆኑ ብዙ ምክንያቶች ትብብሩ ላይ ድርሻ እንዲኖራችሁ እንፈልጋለን። እስካሁን ላለመተባበር የምትሰጡት ምክንያት አሳማኝ አይደለም። ምን አልባት ችግር ሆኗል ብለን የምናስበው ከድርጅቱ መከፋፈል በሗላ በአመራር አካባቢ ባሉ ግለሰቦች መሀል ያለ ጸብ ነው።
2- ያኦጋዴን ነጻ አውጪ ድርጅት። የመካተት እድላቸው የሰፋ ነው። ተገናኝቶ መነጋገርን ይፈልጋል። ከሁሉም ድርጅቶች በታሸለ መሬት ላይ ያለ ትግል ስለምታደርጉ የተጀመረው ትብብር ውስጥ ድርሻ ብታደርጉ አስተዋጿችሁም ሚናችሁም ከፍተኛ ነው።
3- ኦነግ( በዳውድ ኢብሳ የሚመራው። በየትኛውም መስፈርት በጣም ከራቀውና ስህተት ከሆነው አቋማችሁ በተጨማሪ እንደ ኢሀፓ በአመራር ላይ ያሉ ግለሰቦች ጸብ ዋና እንቅፈት የሆነ ይመስለናል። እንዲካተቱ ጥረት መቀጠል ግን አለበት። ተስፋ የሚቆረጥበት ጉዳይ አይደለም። ለአመራሮቹ የቅርብ ጊዜውን ኤኤፍዲን ከዛም በፊት ከወያኔ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሚና ለመጫወት ሞክራችሁ እንደነበር ልናስታውሳችሁ እንፈልጋለን።
ስህተታቸሁ አገራዊና ህዝባዊ ረአይ በጭራሽ ካልነበረውና ፍፁም ላንድ ዘር ወገንታዊ የሆነ ዘረኛ ቡድን ጋር በሽግግር ዲሞክራሲያዊ ስረአትን በመገንባት ከሂደቱ የኦሮሞ ህዝብም እኛም ተጠቃሚ እንሆናለን ብላችሁ ከወያኔ ጋር መተባበራችሁ ነው። ስህተቱን ትልቅ የሚያደርገው ደግሞ ይህን አይነት ቡድን በሁሉም መስክ የበላይነት በያዘበት ሁኔታ ውስጥ የተደረገ መሆኑ ነው። አመኔታን በተመለከተ ለተፈጠረው ክህደትና ብልጣብልጥነት ትልቁ የጥፋት ድርሻ የወያኔዎች ሳይሆን የናንተ ነው።
ለሁላችሁም ጠቅለል አድርገን የምንለው ባጭር ጊዜ ውስጥ እራሳችንን ችለን በተናጠል ወያኔ በአገርና በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ሰቆቃና ጥፋት ልንታደግ በርግጠኝነት በደንብ እንችላለን ካላችሁ ተባበሩ ብለን ጉትጎታችንን ልትረሱት ትችላላችሁ። እርግጠኛ ካልሆናችሁ ግን ለዚህ ግፈኛ ስረአት መቀጠል የሀላፊነት ድርሻ ውሰድ ነው።
በጋራ ለመስራት የመጀመርያውን እርምጃ ለወሰዳችሁ ድርጅቶች እርምጃችሁ ህዘብን ማዳመጥና ሰቆቃ እየተፈጸመበት ያለው ወገናችሁ ህመም እንደሚያማችሁ የሚያሳይ ነው። በተጨማሪም ጊዜው የሚጠይቀውን ፖለቲካ መረዳቱ እንዳላችሁ አስረግጧል። ስለዚህም ምሳጋናችን ከበሬታችንንም እንገልጻለን።
ገና በሂደት ላይ ያለ ብዙ ስራ የሚፈልግ የመጀመርያ እርምጃ እንደሆነ እናውቃለን። ያም ሆኖ ይህን ትልቅ ፖለቲካዊ እርምጃ ለማሳወቅ ጽፎ መበተኑን ብቻ ለምን መረጣችሁ?። ተስማማታችሁ በጽሁፍ ያወጣችሁትን መግለጫ እንኳ ሜዲያዎች ባሉበት በአካል አሰምታችሁት ቢሆን ኖር እርምጃውን ባላሳነሰው ነበር። ለሬሳው ፖለቲካ ተመጣጣኝ መልስ ይሆንም ነበር።
ሌላው ደግሞ ተስማማን እያላችሁ ዬሄን በየግል የምትጠሩትን ህዝባዊ ሰብሰባ ተውት። ህዘብን የበለጠ የሚያምታታና የሚያደክምም እየሆነ ነው። ልዩነታችሁ እንዳል በጋራ ስብስባ ጠርታችሁ በተስማማችሁበት ጉዳይ ማውያየቱ የተሻለ የሚጠቅም ይመስለናል።
በቀጠይ ትብብሩ ምን ቢያደርግ ጠንካራና ለድል ያበቃናል የሚለው ላይ የምናስበውን ማለታችን አይቀርም።
ትብብር ሁላችሁም በተካተታችሁበት በፍጥንት፤ በከፍተኛና፤ ጠንካራ በሆነ ሁኔታ አሁን።