ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከታላላቅ መሪዎች አንዱ መሆናቸውን የአገር ሽማግሌዎች ተናገሩ

‹‹ራዕይ ያለው መሪ ለአንድ አገር ጌጡና ታሪኩ ነው››

ተባባሪ ፕሮፌሰር ታረቀኝ አዴቦ

ዜና ዕረፍታቸው ከተሰማ ዛሬ ስድስተኛ ቀናቸውን የያዙት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አበርክተው ባለፉት ሥራዎቻቸው በኢትዮጵያ ከነበሩትና በዓለም ላይ ካሉት መሪዎች አንዱ ሊሆኑ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ የአገር ሽማግሌዎች ኅብረት አስታወቀ፡፡