የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ግብዓተ መሬት ተፈጸመ

  • ሥርዐተ ቀብሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭት ተላልፏል። (READ IN PDF)

 (ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 17/2004
ዓ.ም፤ ኦገስት
 23/ 2012)፦  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት
ዘኢትዮጵያ ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከአኀት አብያተ ክርስቲያናትና ከሌሎችም የተወከሉ የእምነት አባቶች
በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት ተፈጽሟል፡፡ ሥርዓተ ቀብሩ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ተላልፏል።
ዝርዝር ሐተታውን እንደደረሰልን እናቀርባለን። (Picture: Courtesy of MK Website
የቅዱስነታቸውን ነፍስ በአብርሃምና በይስሐቅ እቅፍ ያኑርልን። አሜን።