አዳማን በተኩስ ያሸበሩት የጥበቃ ሠራተኛ ሁለት ሰዎች ገድለው ሞቱ

በኃያል ዓለማየሁ

አዳማ በሚገኘው በኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ቅርንጫፍ መሥርያ ቤት ያገለግሉ የነበሩት አቶ ጄሉ ሁሌ የተባሉ የጥበቃ ሠራተኛ፣ ከትናንት በስቲያ ከንጋቱ 12፡30 ጀምሮ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የአዳማ ከተማን በመሣርያ ተኩስ ካሸበሩ በኋላ ሁለት ሰዎችን ገድለው እሳቸውም መገደላቸው ተገለጸ፡፡