የቀድሞው የአዋሽ ባንክ ፕሬዚዳንትና አሥር ኃላፊዎች ታስረው በዋስ ተለቀቁ

በታምሩ ጽጌ

የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበርን ከ13 ዓመታት በላይ በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ለይኩን ብርሃኑን ጨምሮ፣ በባንኩ የውጭ ምንዛሪ ዲፓርትመንት ውስጥ ይሠሩ የነበሩ አሥር ከፍተኛ ኃላፊዎች መጋቢት 9 ቀን 2003 ዓ.ም. ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ከትናንት በስቲያ በዋስ ተለቀቁ፡፡