በሁለት ሚሊዮን ብር ጉቦ የተጠረጠሩ ሁለት የፖሊስ ኃላፊዎች ተከሰሱ

–    የወረዳ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት ኃላፊም በክሱ ተካተዋል

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረባ የሆኑ ሁለት የፖሊስ ኃላፊዎችና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ ሁለት አስተዳደር ጽሕፈት ቤት የፍትሕ ኃላፊ፣ ከአንድ ግለሰብ ላይ ሁለት ሚሊዮን ብር ጉቦ ሊቀበሉ ሲሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል በሚል ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡