የዋልድባ ገዳም ህልውና ያሳሰባቸው ኢትዮጵያውያን በጀርመን ሰልፍ አደረጉ
ካለፈዉ መጋቢት ወር አንስቶ ለስኳር ልማት ፕሮጀክት ሲባል ጥንታዊዉ የዋልድባ ገዳምን ይዞታ ይነካል በሚል የተለያዩ ወገኖች ስጋታቸዉን ሲገልፁ ተደምጠዋል። ፕሮጀክቱን የሚመራዉ የመንግስት አካል በበኩሉ የተጠቀሰዉ ፕሮጀክት የገዳሙን ዋነኛ ክፍል እንደማይነካ ነዉ የተናገሩት። ሰሞኑን ደግሞ ይህ ፕሮጀክት የገዳሙን አካል ይነካል የሚል ስጋታቸዉን ለመገናኛ ብዙሃን ካስደመጡ የገዳሙ መነኮሳት አንዱ ለእስር መዳረጋቸዉ፤ ገዳሙም ዉስጥ ወታደሮች መገኘታቸዉ ይነገራል። ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከፍተኛ አካል ስጋታችንን ብንገልፅም ምላሽ አላገኘንም የሚሉት በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች እና ምዕመናን ዛሬ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ፍራንክፈርት ከተማ ላይ ሰልፍ አካሂደዋል። ዘገባውን ያዳምጡ