ጥጥ አምራቾችና ላኪዎች አንድ ቢሊዮን ብር ብድር ሊያገኙ ነው

በውድነህ ዘነበ

የጥጥ እርሻ ባለቤቶች በዚህ ሳምንት ከግብርና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክና ከኒያላ ኢንሹራንስ ጋር በሚያካሂዱት ስብሳባ ምናልባት በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በኮንትራት ስምምነት የሚቀርብ አንድ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ብድር ሊያገኙ እንደሚችሉ የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡