የታክሲዎች የቀጣና ስምሪት ጥናት ተተቸ
– ‹‹አንድ ተራ አስከባሪ በቀን ከ3,000 እስከ 5,000 ብር ያገኛል›› የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
በታምሩ ጽጌበአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በከተማው የሚገኙትን 8,500 ታክሲዎችን በአምስት ቀጣናዎች ለማሠማራት ያጠናው ጥናት የተሟላና ችግርን የሚቀርፍ ሳይሆን፣ ችግሩን ይበልጥ ሊያባብስ እንደሚችል ቢሮው በከተማ አስተዳደሩ መሰብሰቢያ አዳራሽ መጋቢት 8 ቀን 2003 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ተጠቆመ፡፡