የገቢዎችና ጉምሩክ ኦዲተሮች 100 ሺሕ ብር ጉቦ ሲቀበሉ ተያዙ

–    ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሁለት ኦዲተሮች፣ የሒሳብ ምርመራ እንዲያደርጉ ከተላኩበት የግል ድርጅት አንድ ሚሊዮን ብር ጉቦ ጠይቀው 100 ሺሕ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡