ዶ/ር እሌኒ ገብረ መድኅን ለአንድ ዓመት እንደሚቆዩ ማረጋገጫ ሰጡ

–    የምርት ገበያ አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ በዚህ ወር ሥራ ይጀምራሉ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እሌኒ ገብረ መድኅን በምርት ገበያው ለአንድ ዓመት እንደሚቆዩ ማረጋገጫ ሲሰጡ፣ እሳቸውን እንዲተኩ የተመረጡት አቶ አንተነህ አሰፋ፣ ከምርት ገበያው ሠራተኞች ጋር ተዋወቁ፡፡ ከሐምሌ 25 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ ሥራ እንደሚጀምሩ ተገለጸ፡፡