የባለፀጋዋን አገር ዜጋ፤ አቶ ድህነትን እናስተዋውቅዎ
ከዕለታት አንድ ቀን ከምሣ መልስ ቡና የምጠጣበት ካፌ ተሰይሜያለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የአዲስ አበባ መስተዳደር ፕሮግራም ይተላለፋል፡፡ ፕሮግራም አቅራቢያዋ በእኛ ቲቪ ያልተለመደ ዓይነት ፕሮግራም እያቀረበች ነው፡፡ አንዷ መምህርት ትናገራለች ‹‹ልጆቹ ራሳቸውን ይስታሉ›› አለች፡፡ ልጆቹ ያለቻቸው እሷ የምታስተምርበት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎችን ነው፡፡
‹‹እናነሳቸውና ካፌ ወስደን ውሃ አጠጥተን፣ ዳቦ አብልተን ስንለቃቸው ደህና ይሆናሉ፤›› አለች መምህርቷ፡፡ ‹‹በኋላ ላይ ሲደጋገምብን ጠይቀናቸው- ለካስ የሚወድቁት ምግብ ከበሉ ሁለት ሦስት ቀን እየሆናቸው ነው፡፡››
ያንን ፕሮግራም ተመልክተው ከእንባቸው ጋር ያልታገሉ ሰዎች አልነበሩም፡፡ ሕፃናቱ በተለያዩ ምክንያቶች ከወላጆቸቸው የተነጠሉ ሲሆኑ፣ ያልተነጠሉትም ቢሆኑ ቤተሰቦቻቸው በየቀኑ የመመገብ አቅም የሌላቸው ነበሩ፡፡ የኋላ ኋላ በደረሰኝ መረጃ ያንን ፕሮግራም ያቀረበችው ጋዜጠኛ ‹‹በመርዶ ነጋሪነት›› ከአለቆቿ ተግሳፅ ደርሶባታል፡፡
- - -
ኢቴቪ ጫወታ አማረልኝ ብሎ ያቀረባቸው ወጣቶች ናቸው፡፡ ኮሌጅ ዘልቀው ዲግሪ እንደጨበጡ ተናግረዋል፡፡ አሁን ግን በኮብል ስቶን ጠረባ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል፡፡ ኢቴቪ ይሄንን ‹‹ሥራ ፈጠራ›› ብሎታል፡፡ በሥራ ፈጠራና በሥራ አለመናቅ በኩል መስመር አለ፡፡ እነዚህ የተማሩ ኃይሎች፣ የፈለገ ሥራ ባይንቁ እንኳን የተማረ ኃይል እጥረት አለባት የምትባለው አገር ውስጥ ምናልባትም ከዚያ ውጪ ሌላ የሥራ አማራጭ የሌላቸውን ሥራ እየተሻሙ ነው፣ በልተው ለማደር፡፡
- - -
ሰማያዊ ፓርቲ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ፕሮፌሰር መስፍን መወያያ ንግግር አቅርበው ነበር፡፡ ከታዳሚዎቹ አንዱ ‹‹ማስተርስ አለኝ፤›› አለ፡፡ ‹‹ነገር ግን ሥራ አጥቼ በስንት መከራ አሁን አንድ ሺህ ከምናምን ደሞዝ እየበላሁ ነው፡፡ ነገር ግን የክፍለሃገር ልጅ በመሆኔና የቤት ኪራዩን ስለማልችለው ዛሬ አንዱ፣ ነገ አንዱ ጓደኛዬ ቤት እያደርኩ ነው፡፡ ለዚህ ኑሮ ያበቃኝን ኢሕአዴግ እግዚአብሔር ይስጠው›› አለ፡፡ ሪፖርተርም ይህ አይግረማችሁ ሲለን እንዲያውም ‹‹ዲግሪ ያላቸው ዜጎች የጎዳና ተዳዳሪዎች ሆነዋል›› የሚል ዜና አስነብቦናል፡፡
- - -
አንድ መምህር ጓደኛዬን አገኘሁት፡፡ በተለይም እዚህ ከተማ ውስጥ ቤተሰብ ስለሌላቸው መምህራን ባልደረቦቹ ሕይወት ይነግረኝ ገባ፡፡ መምህራኑ ርካሽ ከሚባለው ከት/ቤቱ ካፍቴሪያ ይመገባሉ፡፡ ነገር ግን ተቆራርጣ የምትደርሳቸው ደሞዛቸው በዕዳ ‹‹ኔጌቲቨ›› ትገባለች፡፡ አንዳንዴ ምህረት ይደረግላቸዋል፣ ባብዛኛው ግን ለሚቀጥለው ወር ይሸጋገርባቸዋል፡፡
ጓደኛዬ ሲነግረኝ ‹‹አንዱ፣ የደሞዝ ቀን ዕዳውን ሲያወራርድ 35 ሳንቲም ቀረው፡፡ እሷኑ ሲጃራ ገዝቶ አጨሰባት፡፡›› ይህንን የነገርኩት ሌላ ሰው ‹‹ሲጃራ በ35 ሳንቲም ማግኘቱም ጥሩ ነው፡፡›› አለኝ፡፡
- - -
በጣም ያሳዝናል የኢትዮጵያውያን ህይወት ለዚህ ኑሮ ያበቃንን ኢሕአዴግ እግዚአብሔር ይስጠው
አበስሁ ገበርሁ እረ ጎበዝ የ ኢትዮጵያ ህዝብ ምን ነካው እንደዚህ እየሆነ ስንት ጊዜ ሊኖር ነው ወይኔ ያገሬ ሰው ::
ይህንን ነው መለስ አና ወረበላ ደጋፊዎቻቸው አገር አደገች ተተኮሰች አያሉ የሚያላግጡት የኢትዮጵያ ሕዝብ አድገት ኑሮው የሚለካው አኮ በነሱ ጥጋብ አና የተንደላቀቀ ኑሮ ወይም ለውጭ ጌቶቻቸው ለማሳየት ለልመና አንዲያመቻቸው ተብሎ በደረደሩት ፎቅ አይደለም ባገሪቱ ላይ በሚታየው አውነታ አንጅ ዛሬ ሕዝቡ በገዛ አገሩ ላይ የበይ ተመልካች ሆኖ ለዘመናት ታይቶ በማይታወቅብት መድሎዊ አገዛዝ ውስጥ አየተሰቃየ በአለበት ባሁኑ ሰአት ወያኔዎች በህዝብ ላይ በሚያደርሱት በደል አና ስቃይ ነገ ተጠያቂ መሆናቸው መገንዘብ ይኖርባቸውል ድል ለአትዮጵያ ሕዝብ
Sorry!
ምን ዓይነት ርእስ ነው እባካችሁ ?
ፀሃፊውን እያመሰገንኩኝ 43 ኢትዮጵያውያን በኮንቴይነር ታሽገው ወደደቡብ አፍሪካ በሕገወጥ መንገድ ሲሰደዱ የመሞታቸውን እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው:: ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ከስደት ጋር በተያያዘ ብዙ አሳዛኝ ጉዳቶች በኢትዮጵያውያን ሲደርስባቸው ቆይቶዋል አሁንም እየደረሰባቸው ይገኛል ወያኔ ስልጣን ላይ ከቆየም ይቀጥላል:: ወያኔ በስልጣን ለመቆየት ሲል በፈጠረው የትምክት ፖለቲካ በኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ የህይወት ምስቅልቅል እንዲፈጠር ምክንያት ሆኖዋል:: አሁንም እኛ ኢትዮጵያውያን መታገል ያለብን ለስራ አጥነትና ለስደት ምክንያት የሆነውን የወያኔን ስርአት ብቻ ነው::
Today’s Ethiopian degree and M.Degree are a joke. Our education system lacks quality. No quality at all. Government must regulate the number of degree holders by strengthening the quality of our education system. What we are doing now is irresponsible. We are just giving the seal without knowledge!