በሊባኖስ መሬት ለመሬት የተጎተተችው ኢትዮጵያዊት አስከሬን አዲስ አበባ ገባ

–    የቀብር ሥርዓቷ ዛሬ በትውልድ ሥፍራዋ ይፈጸማል

በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ደጃፍ አጠገብ በአሠሪዋ መሬት ለመሬት ስትጐተትና ስትደበደብ በማኅበራዊ ድረ ገጾች የታየችው፣ በኋላም አወዛጋቢ በሆነ ሁኔታ ራሷን አጠፋች የተባለችው የ33 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ዓለም ደቻሳ አስከሬን ትናንትና አዲስ አበባ ገባ፡፡