ለአዲስ አፍሪካ ማዕከል ግንባታ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲያዋጣ ተወሰነ

ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ይወጣበታል ተብሎ ለሚጠበቀው የአዲስ አፍሪካ ሁለገብ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል የሚውል ካፒታል ለማሳሰብ ለተቋቋመው አክሲዮን ማኅበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ በገንዘብና በዓይነት ለማዋጣት መወሰኑ ተገለጸ፡፡