ከንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ ተዘረፈ

–    ጉዳዩን ፌዴራል ፖሊስ ይዞታል

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በካዛንቺስ ሱፐር ማርኬትና በኢትዮጵያ ልማት ባንክ መካከል ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድነት ቅርንጫፍ መጠኑ ያልታወቀ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ፣ ሰኔ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. ሌሊት መዘረፉን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡