በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የማጥቃት ዘመቻ አሁኑኑ ይጀምሩ!!!
በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን “አምባገነኖችን እየናጠ ያለው ህዝባዊ ማዕበል ወደ አገራችን መቼ ይደርሳል?” በሚል ጉጉት ውስጥ ናቸው። ይህ ጉጉት ተገቢም፤ የሚጠበቅም ነገር ነው። በዚህ ጉጉት መነሻነትም ከየአቅጣጫው የተለያዩ መልእክቶችንና ጥሪዎችን እንሰማለን።
ህዝባዊው አመጽ አገራችን ውስጥ የሚጀመርበት ሁኔታ በአብዛኛው አገር ውስጥ ባሉ ሁኔታዎች የሚወሰን ስለመሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ ብለን እናምናለን።
በውጭ አገራት ያለው ኢትዮጵያዊ ግን አመጹን አሁኑኑ በያለበት አገር ውስጥ ሆኖ ለመጀመር የሚያስችሉ አመቺ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል። የአውሮፓና የአሜሪካ መንግሥታት ለአፍሪቃና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ህዝቦች ከነፃነት ይልቅ መረጋጋትን በመፈለግ ከአምባገነን ገዢዎች ጎን በመቆማቸው የዲሞክራሲ እጦት በህዝቦች ላይ ያስከተለው ምሬት በገዛ ዓይኖቻቸው ለማየት ችለዋል።
የሰሜን አፍሪቃና መካከለኛ ምሥራቅ አብዮቶች ምዕራባዊያን መንግስታትን፣ ታዋቂ የሆኑ የአውሮፓ ተቋማትና ግለሰቦችን ለቅሌት ዳርጓቸዋል። ምሁራንና የቢዝነስ ሰዎች ብቻ ሳይሆን የኪነጥበብ ሰዎችም ጭምር ከአምባገነኖች ጋር በፈጸሟቸው ኮንትራቶች ያገኙትን ትርፍ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች እንዲሰጡ ግፊት እየተደረገባቸው ይገኛል።
በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ይህን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የትግራዩ ገዢ ጉጅሌ ቀንደኛ ደጋፊዎች የሆኑትን ምዕራባዊያን ተቋማትና ታዋቂ ሰዎችን ማጋለጥ መጀመር ይኖርባቸዋል እንላለን። ለመነሻ ያህል የሚከተሉትን በአብነት መጥቀስ ይቻላል።
- ለወያኔ ሹማምንት የትምህርት ማስረጃ ሲያድሉ የቆዩት ምዕራባዊያን የትምህርት ተቋማት ዝርዝራቸው መታወቅ ይኖርበታል። ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገኙ የሲቪክ ማኅበራት እነዚህ ተቋማት ከአምባገነን የኢትዮጵያ ገዢዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በአስቸኳይ እንዲያቋርጡ ማሳሰቢያ ሊጽፉላቸው ይገባል። ተቋማቱ አፋጣኝ ምላሽ ካልሰጡ የተቋሟቱን ተግባር ለተማሪዎቻቸውና ሌሎች ደንበኞቻቸው ማሳወቅ ይገባል። ይህ ዓይነቱ ተግባር የተቋማቱን ስም የሚያጎድፍ በመሆኑ ፈጣን ምላሽ እንደሚያስገኝ መገመት ይቻላል። በተለይም የብሪታኒያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሰሜን አፍሪቃ አምባገነኖች ጋር በነበራቸው የቢዝነስ ግኑኝነት ሳቢያ ቅሌት ውስጥ የገቡበት ጊዜ በመሆኑ የማጥቃት ርምጃው ውጤታማ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው፤ መፍጠን ይኖርብናል።
- የክፋት ቁንጮ ከሆነው መለስ ዜናዊ ጋር ልዩ የጥቅም ወዳጅነት የፈጠሩ ታዋቂ ሰዎች በአውሮፓና አሜሪካ አሉ። አንዳንዶቹ (ለምሳሌ እንደ ጀፈሪ ሳክስ እና ቶማስ ስቲግሊክስ ያሉ) በሙያቸው ከበሬታን ያገኙ ሰዎች ናቸው። ሌሎች ደግሞ የፓለቲካ ሰዎች ወይም በጎ አሳቢዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ከአምባገነኖች ጋር መሞዳሞድ የእነሱ የግል ክብር እና ሙያቸውን የሚያጎድፍ መሆኑ ጥርጥር የለውም። ይህንን እንዲያውቁ እና ራሳቸውን ከመለስና ቡድኑ እንዲያርቁ በማያሻማ ሁኔታ ሊገለጽላቸው ይገባል። አለበለዚያ የራሳቸውን ክብር የሚያጡ መሆኑን ማሳሰብ ይገባል።
- ከኢትዮጵያ አምባገኖች ጋር የኮንትራት ሥራ ሠርተው ገንዘብ የተቀበሉ ተቋማት “የደም ገንዘብ” ነክተዋልና ከኮንትራቱ ያገኙትን ትርፍ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች እንዲሰጡ ማስጨነቅ ይገባል። ቢዝነስ በስነምግባር መመራት አለበት። ከመለስ ዜናዊ አገዛዝ ጋር የነገዱትን ሁሉ በሙስና የምንጠረጥራቸው በመሆኑ ራሳቸውን እንዲያጠሩ እንንገራቸው።
- የትግራዩ ገዢ ጉጅሌ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በውጭ አገራት ውስጥ የሚያካብቱትን ሃብትና ንብረት መከታተል፤ ቤቶቻቸውን መያዝ፤ በንግዶቻቸው ላይ ማዕቀብ መጣል፤ በየሄዱበትና በየደረሱበት ማስነወር በተከታታይና በተደራጀ መልክ ሊሰራ የሚገባ ተግባር ነው።
- በኢንተርኔትም የጥቃት ዘመቻ መጀመር ይኖርበታል። በፌስ ቡክ የተጀመረው ዘመቻ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ቢሆንም በቂ ነው ማለት አይደለም። ፌስ ቡክ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊዘጋ ይችላል ብሎ በማሰብ አማራጭ ሊፈለግ ይገባል። የኢንተርኔት አገልግሎት የሌላቸው ወገኖቻችንን እንዴት ልንደርሳቸው እንደሚገባም ሊጠና ይገባል።
- በቴሌቪዥንና በሬድዮ የተጀመረው ዘመቻ በከፍተኛ ሁኔታ ማጠናከር ይገባል። ኢሳትን ማጠናከር የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ኃላፊነት መሆን ይኖርበታል።
- በየአገሩ ኢትዮጵያዊያን የሚያደርጓቸው የተቃዉሞ ሰልፎች ተጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል።
ግንቦት 7 ጥቃቱን የተሳካ ለማድረግ የወጣቶች የፈጠራ ችሎታ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረግ እንደሚችል ከፍተኛ እምነት አለው። ወጣቶቻችን የትግራዩ ገዢ ጉጅሌን የመረጃ አፈና የሚበጣጥሱበት መንገድ አያጡም ብሎ ያምናል። ይህን የፈጠራ ችሎታ መጠቀሚያ ወቅት አሁን ነው።
በውጭ አገራት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ዓይኖቹን ከአገር ቤት ሳይነቅል ህዝባዊ አብዮቱን በያለበት አገር ዛሬውኑ ይጀምር!!! አሁን ማጥቃት ላይ ነን፤ በኅብረትና በጽናት እናጥቃ!
በቃ -ጋዮ