የእስልምና ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ነዉ ተባለ

በኢትዮጵያ እስልምና ዙሪያ የሚነሱ አነጋጋሪ ጥያቄዎች የመፍትሔ ሃሳብ ሃሳብ የሰጡ ሁለት ምሁራን፣ በእዉቀት ላይ የተመሰረተ መሪነት የሚሰጥ የሃይማኖት ተቋም ማቋቋም አሁን በሃይማኖቱ ዙሪያ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚካሄደዉ ዉዝግብ አይነተኛ መፍትሔ ነዉ ብለዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና የባህል ረዳት ፕሮፌሰር አቶ አህመድ ዘካሪያና በእስልምና ጉዳዮች ዙሪያ ብዙ መጽሐፊችን የደረሱና ብዙዎችንም የተረጎሙ አቶ አቶ ሀሰን ታጁ፣ በኢትዮጵያ የእስልምናን ፓለቲካዊና ማህበራዊ ታሪክ፣ በወቅቱ በሃይማኖቱ ዙሪያ ዉዝግብ የሚሰማበትን ምክንያትና የመፍትሔ ሃሳብ በየበኩላቸዉ አስተያዬት ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር እስከ ሺ974 ዓም በአንድ ሃይማኖት የበላይነት የሚያምንና ሌሎቹን በመጨፈለቅ፣ በተለይም እስልምናን በመምታት ላይ የተመሰረተና ድጋፍ ያገኝ የነበረዉም ከቤተክህነት እንደነበር ተናግረዋል።

ማህበራዊ የሙስልሞችና የክርስትና እምነት ተከታዮች ማህበራዊ ግንኙነት ግን ከፓለቲካዉ በጣም የተሻለና ተሳስቦ የመኖር ታሪክ የሚያንጸባርቅ መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን በኢትዮጵያ እስልምና ዙሪያ ለተከሰቱ ጥያቄዎችና ዉጥረቶች ምሁራኑ ከሶሻልዝም ርእዮተ ዓለም ዉድቀት በሁዋላ በዓለም ዙሪያ የህዝቦችን ወደ ሃይማኖት መመለስ አዝማሚያ፣ የኢንተርኔት የሌሎች የመገናኛ ብዙሃን መስፋፋት ሙስልሞች ሃማኖታቸዉን እንዲያዳብሩ ማስቻሉን አመልክተዋል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከሁለቱ ምሁራን ጋር የተደረገዉን ሰፋ ያለ ዉይይት እንድታዳምጡ እንጋብዛለን።