የማስታወቂያ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ
• ተጠቃሚ ሳይፈቅድ የንግድ ማስታወቂያ በተጠቃሚ ስልክ አይሰራጭም • የጋዜጦች የማስታወቂያ ሽፋን ከ70 በመቶ መብለጥ የለበትም • የውጭ ማስታወቂያ በቅድሚያ በአገሪቱ ፊደል መጻፍ አለበት • ጋዜጠኞች በጣቢያቸው ማስታወቂያ ማንበብ አይችሉም
በተለያዩ መንገዶች የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች በሕግና በሥርዓት እንዲመሩ ለማድረግ ያስችላል የተባለለት ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡ አዋጁ በማስታወቂያ ሥራ የመሰማራት መብትን በትውልድ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ የውጭ አገር ዜጎችም ሰጥቷል፡፡