መፍትሔ የታጣለት የትራፊክ አደጋ

ከጥቂት ዓመታት በፊት ለመጀመርያ ጊዜ ኢትዮጵያን የጎበኘ አንድ ኡጋንዳዊ ጦማረኛ፣ በስብሰባ ምክንያት አዲስ አበባን ሲጎበኝ ከታዘባቸው ጉዳዮች አንዱ ዘመን ጠገብ  ተሽከርካሪዎች በየጎዳናው ሲንፏለሉ አግራሞትን የሚጭሩ እንደሆኑ በጦማሩ አስፍሮ ነበር፡፡