ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ ዞን ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ
• ነገ ለውይይት ይቀርባል
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በመላ አገሪቱ ከሚገኙ የከተማ አስተዳደሮች ለኢንዱስትሪ ዞን ግንባታ የሚሆኑ ቦታዎችን በውክልና ተረክቦ ለአልሚዋች የሚሰጥበት ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ፡፡ ሚኒስቴሩ በዚህ የሕግ ማዕቀፍ ዙሪያ ከክልልና ከፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ጋር ለመምከር ለሰኞ ሰኔ 18 ቀን 2004 ዓ.ም. ስብሰባ ጠርቷል፡፡