የሸራተን አዲስ ሆቴል ሁለት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ለቀቁ

– የስድስት ሚሊዮን ብር ‹‹ስዊች ጊር›› ሊወጣ ሲል ተያዘ

በታምሩ ጽጌ

በሸራተን አዲስ ሆቴል ለረጅም ዓመታት በከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ላይ የነበሩት የሆቴሉ ምክትል ሥራ አስኪያጅና የሰው ሀብት ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ከመጋቢት 5 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራቸውን መልቀቃቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡