አቶ መለስ ይቺን ጽሑፍ ቢያነብልኝ ዕድለኛ ነኝ
ፍቅር ይበልጣል
አሁን ይህችን ጽሑፍ ስከትብ አዲስ አበባ አካባቢ ዝናብ እያካፋ ነው። በውጭ ለምትኖሩ ይህ ወሬ መልካም ዜና ነው። ፀሐይዋ አናት እየበሳች ተቸግረን ከረምን። የዝናብ መጥፋት በቅድሚያ ለእህል ዘር መጥፎ ነው። ቀጥሎም የአካባቢ ሙቀትን በመጨመር ለአየር ንብረት መዛባትና ለበረሃነት መስፋፋት እንዲሁም ለሰውና ለእንስሳት ሕይወት መጥፎ ነው። አሳስቦን ነበር ተመስገን። በዚሁ ያዝልቅልን። በሁሉም መበደል አይገባንም።