በሁለት ሳምንት ውስጥ መንግሥት 100 ሺሕ ቶን የምግብ ዘይት ሊያስገባ ነው

በኃያል ዓለማየሁ

በአገሪቱ ውስጥ ከዘይት መጥፋት ጋር እየጨመረ የመጣውን የዘይት ፍላጎት ለማሟላት፣ መንግሥት በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ 100 ሺሕ ቶን የምግብ ዘይት (ፓልም ኦይል) የሚያስገባ መሆኑን፣ በንግድ ሚኒስቴር ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አማከለ ይማም ለሪፖርተር ገለጹ፡፡