በጨለማ ያለ ህዝብ ብርሃን ያያል


በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።  በጨለማ ውስጥ ያለ ሕዝብ ብርሃን ያያል

በጨለማ ያለ ህዝብ ብርሃን ያያል

በኢትዮጵያ ውስጥ በማናቸውም ዕምነት ውስጥ የፖለቲካ ዝናር የታጠቁ፣ ምንደኛ ቃየላዊያን የሰው ልጅ ነጻነት፣ ወደማይፈቅደው የጨለማ ጎዳና ቢያንገላቱትም የራሳቸው የክህደት ፈጠራ እንዳነገቡ ወደ ጥልቁ ወውረዳቸው የማይቀርና በጨለማ ያለው የኢትዮጵያ  ሕዝብ ብርሃን የሚያይበት ቀን ሩቅ አይሆንም።

መሰሪዎቹና የመለያየትና የተንኮል ትምህት ተባባሪዎቻቸውም በንቀትና በማጣጣል “ጨርቅ” ያሏት የጥቁር ሕብቦች የነጻነት ምልክት የእናት ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ/ ባንዲራ (አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ) የፍርዷ ቀን ደርሶ በአቶ መለስ ዜናዊና በግብረአበቻቸው ላይ ያ “ወራዳ” ያሉት ሕዝብ የነጻነቱን የጩኽት ድምጽ በዓለም አደባባይ ወራዳነታቸውን አንገታቸውም በመድፋት ራሳቸው አቶ መለስ ዜናዊ ያረጋገጡት እውነታ ነው። ይህንን ይመልከቱ። http://www.youtube.com/watch?v=hUVsq-FDFRE&feature=relmfu

ስለሆነም የኢትዮጵያን የነጻነት እሳት ለመገደብም ሆነ ለማጣጣል የሚዳዱ ቢኖሩ “በቃኝ “ ሲል የኢትዮጵያ ሕዝብ  ምን ሊያደርግ እንደሚችል የረዥም ዘመናት ታሪኩን ያልተገነዘቡ አሊያም በክህደት የቆሙ ብቻ ናቸው። ይህ በምድረ አሜሪካ በአምባገነኖች ላይ ያስተጋባው የኢትዮጵያ ነጻነት (Freedom) ጩኽት ድምጽ በቅብብሎሽ በኢትዮጵያ ብቻ አይደለም በሌሎችም የዓለም አገሮች ማስተጋባቱን ቀጥሏል። (እግዚያብሔር ይመስገን)። በመሆኑም ከዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ጩኽት ድምጽ ቅብብሎሽ ተቃራኒ የሆነ አሰራር ይዞ ኢትዮጵያን ልምራ ወይንም ለኢትዮጵያ አውቅላታለሁ የሚል ማናቸውም ቡድን ከጠላት እንጅ ከወዳጅ እንዳልሆነ ሁሉም አገር ወዳድ ልብ ሊለው ይገባል።

የዚህ የነጻነት ጩኽት ቅብብሎሽ በሁሉም መስክ ለኢትዮጵያ ነጻነት በሚጠሩ ማንኛውም ህዝባዊና ሰላማዊ የተቃውሞ ትዕይንቶችና ሰልፎች ወይም ስብስቦች ላይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በአንድ ላይ፣ በአንድ ጥላ ስር የማያሰባስብና የማያሳትፍ፣ እንቅስቃሴና ጥሪ ውጤት አልባ ከመሆኑም በላይ በአገሪቱ ላይ እንደ አልቅት ተጣብቆ ደሟን የሚመጠውን የመለስን አገዛዝ ዕድሜ ማራዘምም ነው የሚሆነው። የአቶ መለስ አምባገነን አገዛዝ የኢትዮጵያዊነትን ብሔራዊ ስሜትና ራዕይ ከትውልድ ጭንቅላት ሰርዞ ሊቆራርጡንና ሊያቆራርጡን ቢዳክሩም ኢትዮጵያዊያን የአንድ እናት ልጆች መሆናችንን ሊገቱት  ከቶ አልቻሉም።ይልቁንም ኢትዮጵያ ወይም ነጻነት ብለን አንገታቸውን አስደፍተናቸዋል።  በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ጩኽት ድምጽ ቅብብሎሽ እንደ ሰደድ እሳት በሁሉም  ቦታና ጊዜ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ይቀጥላል።

ሀቁን ተረድተው ጥፋቱን ከማረም ይልቅ እርስበርስ እንድንለያይና እንድንበላላ፣ እንድንገዳደልና እንዳንተማመን የሚያደርጉንና የፈጠሩትን ፖሊሲ ለራሳቸው ለአቶ መለስና ለአገዛዛቸው አከናንበን የኢትዮጵያዊ የፍቅር አንድነታችንን የበለጠ ገንብተን በክብር ለማለፍ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በማናቸውም መስክ ድምጹን እንዲያሰማ በሚደረገው ተግባራዊ ውጤታማ ሥራ በጨለማ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ብርሃን ያያል።

ከመሬት የኢትዮጵያ ህዝብ ንቅናቄ