በጨለማ ያለ ህዝብ ብርሃን ያያል


በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።  በጨለማ ውስጥ ያለ ሕዝብ ብርሃን ያያል

በጨለማ ያለ ህዝብ ብርሃን ያያል

በኢትዮጵያ ውስጥ በማናቸውም ዕምነት ውስጥ የፖለቲካ ዝናር የታጠቁ፣ ምንደኛ ቃየላዊያን የሰው ልጅ ነጻነት፣ ወደማይፈቅደው የጨለማ ጎዳና ቢያንገላቱትም የራሳቸው የክህደት ፈጠራ እንዳነገቡ ወደ ጥልቁ ወውረዳቸው የማይቀርና በጨለማ ያለው የኢትዮጵያ  ሕዝብ ብርሃን የሚያይበት ቀን ሩቅ አይሆንም።

መሰሪዎቹና የመለያየትና የተንኮል ትምህት ተባባሪዎቻቸውም በንቀትና በማጣጣል “ጨርቅ” ያሏት የጥቁር ሕብቦች የነጻነት ምልክት የእናት ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ/ ባንዲራ (አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ) የፍርዷ ቀን ደርሶ በአቶ መለስ ዜናዊና በግብረአበቻቸው ላይ ያ “ወራዳ” ያሉት ሕዝብ የነጻነቱን የጩኽት ድምጽ በዓለም አደባባይ ወራዳነታቸውን አንገታቸውም በመድፋት ራሳቸው አቶ መለስ ዜናዊ ያረጋገጡት እውነታ ነው። ይህንን ይመልከቱ። http://www.youtube.com/watch?v=hUVsq-FDFRE&feature=relmfu

ስለሆነም የኢትዮጵያን የነጻነት እሳት ለመገደብም ሆነ ለማጣጣል የሚዳዱ ቢኖሩ “በቃኝ “ ሲል የኢትዮጵያ ሕዝብ  ምን ሊያደርግ እንደሚችል የረዥም ዘመናት ታሪኩን ያልተገነዘቡ አሊያም በክህደት የቆሙ ብቻ ናቸው። ይህ በምድረ አሜሪካ በአምባገነኖች ላይ ያስተጋባው የኢትዮጵያ ነጻነት (Freedom) ጩኽት ድምጽ በቅብብሎሽ በኢትዮጵያ ብቻ አይደለም በሌሎችም የዓለም አገሮች ማስተጋባቱን ቀጥሏል። (እግዚያብሔር ይመስገን)። በመሆኑም ከዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ጩኽት ድምጽ ቅብብሎሽ ተቃራኒ የሆነ አሰራር ይዞ ኢትዮጵያን ልምራ ወይንም ለኢትዮጵያ አውቅላታለሁ የሚል ማናቸውም ቡድን ከጠላት እንጅ ከወዳጅ እንዳልሆነ ሁሉም አገር ወዳድ ልብ ሊለው ይገባል።

የዚህ የነጻነት ጩኽት ቅብብሎሽ በሁሉም መስክ ለኢትዮጵያ ነጻነት በሚጠሩ ማንኛውም ህዝባዊና ሰላማዊ የተቃውሞ ትዕይንቶችና ሰልፎች ወይም ስብስቦች ላይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በአንድ ላይ፣ በአንድ ጥላ ስር የማያሰባስብና የማያሳትፍ፣ እንቅስቃሴና ጥሪ ውጤት አልባ ከመሆኑም በላይ በአገሪቱ ላይ እንደ አልቅት ተጣብቆ ደሟን የሚመጠውን የመለስን አገዛዝ ዕድሜ ማራዘምም ነው የሚሆነው። የአቶ መለስ አምባገነን አገዛዝ የኢትዮጵያዊነትን ብሔራዊ ስሜትና ራዕይ ከትውልድ ጭንቅላት ሰርዞ ሊቆራርጡንና ሊያቆራርጡን ቢዳክሩም ኢትዮጵያዊያን የአንድ እናት ልጆች መሆናችንን ሊገቱት  ከቶ አልቻሉም።ይልቁንም ኢትዮጵያ ወይም ነጻነት ብለን አንገታቸውን አስደፍተናቸዋል።  በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ጩኽት ድምጽ ቅብብሎሽ እንደ ሰደድ እሳት በሁሉም  ቦታና ጊዜ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ይቀጥላል።

ሀቁን ተረድተው ጥፋቱን ከማረም ይልቅ እርስበርስ እንድንለያይና እንድንበላላ፣ እንድንገዳደልና እንዳንተማመን የሚያደርጉንና የፈጠሩትን ፖሊሲ ለራሳቸው ለአቶ መለስና ለአገዛዛቸው አከናንበን የኢትዮጵያዊ የፍቅር አንድነታችንን የበለጠ ገንብተን በክብር ለማለፍ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በማናቸውም መስክ ድምጹን እንዲያሰማ በሚደረገው ተግባራዊ ውጤታማ ሥራ በጨለማ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ብርሃን ያያል።

ከመሬት የኢትዮጵያ ህዝብ ንቅናቄ

5 Comments on “በጨለማ ያለ ህዝብ ብርሃን ያያል”

  1. ይህንን መግለጫ ያወጣችሁ እጃችሁን ይባርከው ለማለት እወዳለሁ። ይህንንም ለማለት ያስቻለኝ ምክንያት አፍቃሪ ወያኔ የሆነው እራሱን “ማህበር ቅዱሳን” እያለ የሚጠራው ቡድን ይህንን ሰሞን በኢሳት ላይ የዋልድባን ገዳም አስመልክቶ በማስነገር ላይ ያለው የሰላማዊ ሰልፍ ማስታወቂያ ነው። የሰልፉ ጥሪ ነጥሎ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን ከነሱም ውስጥ “የቁርጥ ቀን” ልጆች ብሎ የሚጠራቸውን ብቻ ሲሆን የፕሮቴስታንት ክርስትና አማኞችንና የካቶሊክ ክርስትና አማኞችን አይጋብዛቸውም። የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያንን ስማቸውንም አያነሳም። ኢትዮጵያውያን የቤተ እስራኤል (ኦሪት አማኞች) ከመፈጠራቸውም አያውቃቸውም። እንዲሁም የተለያዩ ባሃላዊ እምነት ተከታዮችንና ከነጭራሹም እምነት የሌላቸውን ኢትዮጵያዊንን አይጠቅሳቸውም። ታዲያ በአሁን ሰዓት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሃይማኖት፣ ዘርና አካባቢ ሳይለይ ቀፎው እንደተነካ ንብ በአንድ ላይ ወያኔ ላይ ባነጣጠረበት ጊዜ ከፋፍሎና ነጣጥሎ ጥሪ ማድረግ ምን ማለት ነው? ይህ የለየለት የመለስ ዜናዊ ስራ ከመሆን ያለፈ አይደለም። ከዚህም በተጨማሪ ለምንድን ነው ለዋልድባ ገዳም ብቻ የምንጭኽው? ዝቋላ ገዳምስ? አሰቦትስ? አርሲ ገዳብ አሳሳ በወያኔ የፈሰሰው የንጹሃን ሙስሉሞች ደምስ? ሃይማኖቴን አላስበርዝም አላስከልስም በማለት ከፍተኛ ትግል በማድረግ ላይ ያለው መላው ኢትዮጵያዊ ሙስሊምስ? በመታረድ ላይ ያሉትንስ አኝዋኮችስ? ቁምስቁሉን በማየት ላይ የሚገኘው የአፋርስ ህዝብስ? ከቀየው በመባረር ላይ የሚገኘውስ የአማራ ተወላጅስ? በውስጥ እየነደደ ያለውና በስሙ የሚነገድበትስ የትግራይ ተወላጅስ?በአጠቃላይ ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝብ አሳሩን በመቁጠር ላይ ይገኛል። ሁሉም አገሩ ነውና በኢትዮጵያዊነቱ ሊጋበዝ ይገባዋል። ጥሪው ሁሉንም ሊዳስሰው ይገባል። ስለሆነም ተካፋፍሎ የሚደረግ ማንኛውም ሰልፍ ላይ መሳተፍ ወያኔን መጥቀም ነውና ማንኛችንም በነዚህ ዓይነት ጥሪዎች ላይ መሳተፍ የለብንም። ኢሳቶችም ይህንን አይነት በመርዝ የተጠቀለለ ማር ወደ ህዝብ ከማቅረባችሁ በፊት ጥንቃቄ መውሰድ ይገባችሁ ነበር፤ የሚሰራ ሰው ይሳሳታልና በአስቸካይ ማስታወቂያውን በማቋረጥ የእርምት እርምጃ መውሰድ ይገባችዃል።

  2. ድሪባ ታሳዝናለህ; ይህ ለሁሉም ነው ግና ሌሎች ሁልጊዚ ወደ ህዋላ እያሉ ቢተ ክርስቲያን እስከምተፋ ነው የሚተብቁት

  3. ዽሪባ እጅግ አመሰግናለሁ:; እራሱን ቅዱስ ነኝ ብሎ የሚጠራው ማሕበር የወያኔ ባርያ ለመሆኑ ስራው ምስክር ነው:; የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኝ ብንድ ላይ እንዳይቆም ህዝቡን በመከፋፈል ታላቁን የሀገርና የሃይማኖት ጥፋት ፈጽሞ አሁን ደግሞ ሲያሳድዳቸው የነበሩትን የዋልድባ አባቶች አፍቃሪ በመምሰል ህዝቡን ለመነጣጠል ኦርቶዶክሱን ብቻ ለተቃውሞ ሰልፍ ጠርቶ ሊከፋፍለን እየሮጠ ይገኛል:; ይህ ያባ ጳውሎስ ውሻ በመላው አለም የሚገኙትን ቤ/ክ ከፋፍሎ ለጌታው ስጦታ አቅርቦናል:; አሁንም ይህን የማፍያ ቡድን ነቅተን እንጠባበቀው:; ተጸጽተው ወደልቦናቸው ካልተመለሱወና ይህን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ካልተቀላቀሉ ዘላለማዊ የቤ/ክ እና የ ህዝብ ጠላቶች እንደሆኑ ይቀጥላሉ:; ዋልድባ የኦርቶዶክስ እምነት ቅዱስ ቦታ ቢሆንም ንብረትነቱ እና ታሪካዊነቱ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ስለዚህ ሁሉንም ይመለከታልና ጥሪው ሁሉን አቀስ መሆን ይገባው ነበር:; ኢሳቶች ይህን ከፋፋይ ቡድን በጥንቃቄ ተመልከቱት:; የጠላቴ ጠላት ወዳጀ ነው ብላችሁ ሊሆን ይችላል ግን ይህ ቡድን የጠላታችን የእያኔ ወዳጅ እንጅ ጠላት እንዳልሆነ ስራውን ተመልከቱ:; እኔን ስለማታውቁኝ ላታምኑ ትችላላችሁ እስኪ አቡነ መልከጸዲቅን ስለዚህ ማህበር ጠይቁአቸውና ምን እንደሚሉ ከሳቸው ተረዱ:; ይህ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ በተጀመረው ያንድነት እንቅስቃሴ ሰርጎ እንዳይገባ በጣም መጠንቀቅቅ አለብን

  4. እውነትም መሬት ቸር ወሬ ያስማን:: ሁሉም በመሬት ላይ ነው:: በርቱ ….

  5. ከእግዚአብሔር ለሰው ልጆች የተሰጠን አእምሮ አለን።ይህም ክፉንና ደጉ ነግር እንድንለይበት ነው። ስለ ሃይማኖታችን ስንነጋገር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መሆን ይገበዋል። ዛሬ ዛሬ የሚናየውና የምሰማው የክርስቲናዊ ህይወት በኦርቶዶክስ እምነት ሽፋን የሚደረጉት እንቅስቃሴና ጉዞ ግን ብዙውን የእምነቱ ተከታዮች እጅግ እያሳዘነ ነው። ኢትዮጵያ ህዝቦቿ እጆቻቸውን ወደ እግዚአብሔር ይዘረጋሉ። መዝ 68 ቁ 31

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*