መለስ አለምላስ! ”ነጻነትን” ብሎ የጮህው ወገን

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሃገሬ)

በሜይ 18 2012 መለስ ዜናዊ በማይዋጥለትና ጨርሶ እስከመቃብሩ ድረስ ሊረሳው የማይችለውን ትምህርት ቀሰመ። በነጻው ሃገር፤ ሃሳብን ያለምንም ገደም መግለጽ በሚቻልበት ነጻ ምድር፤ መለስ አፉ ተለጎመ። ያ ያለገደብ ባሻው መልኩ ስድብና ነቀፌታ፤ ፌዝና ሽሙጥ፤ ተራ ክብረ ነክ ቃላት ሲተፋ የነበረው አንደበቱ ታሰረ። በዋሺንግቶን ከተማ የሚኖረው ወጣት ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ አበበ ገላው፤ በጂ8 ስብሰባ መሃል ስለ አፍሪካ የምግብ ዋስትና ላይ በተካሄደው ውይይት መሃል ብድግ ብሎ አዳራሹን ባናወጠው ድምጽ ሲናገር መለስ ዜናዊ አይኑ ፈጦ ቀረ። የአበበ ገላው ሃያል ድምጽ አስተጋባ:-