ማን ይሁን እውነተኛ? “ለማህበረ- ቅዱሳን” የተሰጠ ምላሽ:
የሀገሬ ሰው ቅጥፈት የለመደች እጅ ከንስሃ ይልቅ ለዓመጽ ቅርብ ነች እንዲል ይህ ነፍሰ ገዳይ ሳለ ራሱን “ማህበረ ቅዱሳን” በማለት የሚጠራ ስሙ የማይጠራ የነገሰበት የጎበዝ ስብስብ በስህተት ላይ ስህተት፣ በውሸት ላይ ውሸት፣ በአመጽ ላይ አመጽ መስራትና መደጋገም ሁነኛ መታወቂያው ለመሆኑ ማናችንም አንስተው። ይህን መሰሉ የማህበሩ (“የማህበረ ቅዱሳን”) መሰሪ ድርጊት በማጋለጥ ረገድም ጸሐፊው “ደጀ ሰላም” በመባል የሚታወቀው የሽብርና የሁከት ማእከል መካነ ድሩ “የማህበረ ቅዱሳን” ለመሆኑና ማህበሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያንና አገልጋዮችዋን ማተረማመስ እንዲሁም ማሳደድ በተቀናጀ መልኩ እየተያያዘው ሲመጣ የቀድሞ ስራዎቹ (ባለቤትነቱን የሚመሰክሩና የሚያረጋግጡ) ከስፍራው በመቀል የእኔ አይደለም በማለት እስከመካድ ደርሶል። በዚህም ሳይመለስ የሚያቀኝ የለም በሚል የሞኝ ፈሊጥም እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ ያለውንና የሌለውን አቅም በመጠቀም ከወትሮ በበለጠ ሁኔታ ሰማያዊትና ቅድስት በሆነችው ቤ/ያን ላይ ሽብርንና ሁከትን በመዝራት ረገድ እየገፋበት እንደሚገኝ በማከል ከጥቂት ቀናት በፊት የሚከተለውን ለንባብ መብቃቱ ይታወሳል።
“ይህ የሚመለከቱት መረጃ “ደጀ ሰላም” በመባል የሚታወቀውን ድረ-ገጽ/ብሎግ ሲጀመር ማኅበሩ የራሱ እንደሆነ በይፋ በድህረ ገጹ የገለጸበት/ያስተዋወቀበት በእንግሊዝኛ የድረ-ገጹ የመጀመሪያ የጽሑፉ “ሊንክ” ነበር። በተለይ deje-selam.blogspot.com/…/Ethiopia-mahberekidusan-eotc-past.html- የሚለውን ጽፈው ለመጎልጎል የሞከሩ እንደሆነ “ጭራሽ ከስፍራው ተነቅለዋል” የሚል መልስ ነው የሚያገኙ ለምን? ማኅበሩ ስራዬ ብሎ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን መዋጋትና ማፈርስ ብሎም ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንና የአባቶችን ክብር በሚነካ መልኩ ከአንድ በኢትዮጵያዊ ባህልና ወግ ያደገ ፍጡር በማይጠበቅ ልቅነትና ዋልጌነትን በእጅጉ አይለው በሚታዩበት ሁኔታ ማዋረድና ማንቋሸሽ እየተያያዛው ሲመጣ ጽሑፉን ከስፍራው በመንቀል የእኔ አይደለም እስከማለት ደርሰዋል።” ታድያ ይህን ቁልጭ ያለውን በማያሻማ አገላለጽና ግልጽ መርጃ/ሰነድ የተደገፈውን ሐቅ ሽምጥጥ አድርገው ለመካድ የሆነውና ያልሆነውን ያልተባለና ያልተጠየቁትም ለመቀባጠር እንቅልፍ አጥተው ሰንብተው ኖሯል። በዚህ አጋጣሚ “… ምላሽ” በማለት የቀረበውን የቅጥፈት ስራ ሳይውል ሳያድር በኢ-ሜይል አድራሻዬን የላክልኝ ወዳጄ መ/ም ደመላው እጅግ አድርጌ ላመሰግንህ እወዳለሁ።
ውድ አንባቢ! “ልሳነ ሌዋታን “ደጀ ሰላም” የማን ናት!” በሚል ርዕስ የቀረበውን እውነት ለማደፋን “ደጀ ሰላም” የማ/ቅዱሳን ናት በሚል “ኢትዮፕያንሪቪው” ላይ ለተስተናገደው ጽሑፍ የተሰጠ ማስረጃዊ ምላሽ” በሚል በመካነ ድሩ በኩል “አይደለም! ሐሰት ነው የተሃድሶዎች ውንጀላ ነው” ሲል ሀፍረት ሳይሰማቸው ዳግም ለማደናገር ቃጥታቸውል። ታድያ ዲ/ን ሙሉጌታ ለቃላቸው እማኝ በዋናነት በማስረጃነት ያቀረቡትን “ሊንክ” (deje-selam.blogspot.com/…/Ethiopia-mahberekidusan-eotc-past.html-) ተጭነው እውነቱ እንዲያረጋግጡ በተጠየቀው ጥያቄ መሰረት ነው ማላሹ የተሰጠ ወይስ ሃሳባቸውንና ሐተታቸውን “ደጀ ሰላም” “የማህበረ ቅዱሳን” ለመሆኑ አክለው በተጻፉ ላይ? መካነ ድሩ “የማህበረ ቅዱሳን” የሚገልጽና የሚያሳይ ማህበረ ቅዱሳን “ደጀ ሰላም” መካነ ድር የእኔ ነው ሲል ያስተዋወቀውና ራሱ ያስተዋወቀበትን በጸሐፊው ለመረጃ የቀረበውን ሊንክ የት ገባ? ለምንስ መልስ ሳይሰጥበት ተዘለለ? መካነ ድሩ “የማህበረ ቅዱሳን” ለመሆኑ በማያሻማ መልኩ የሚያሳይ ተብሎ በብቸኛነት ማስረጃ የቀረበው እኮ (deje-selam.blogspot.com/…/Ethiopia-mahberekidusan-eotc-past.html-) የሚለውን ነው? ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ይሉት እንዲህ ያለውን ነው።
እንግዲህ ጎግልም “የተሃድሶ” ነው! ካልተባለ በስተቀር ቀድሞ የሰጡትን ቢጠይቁት ያለውን የሚሰጥዎት የሚያረጋግጠው ሐቅ ይህ ነው። “ደጀ ሰላም” የምትባለውን ልሳነ ሌዋታን የግብረ እከዩ ድርጅት “የማህበረ ቅዱሳን” ለመሆንዋ የሚከተለውን “ሊንክ” ጎግል በሚባለው ገጽ ላይ አስፍረው ይጨቁኑትና እውነቱን ይለዩ። “(deje-selam.blogspot.com/…/Ethiopia-mahberekidusan-eotc-past.html-)
ጎግል የዋዛ አይደለም! የተባለውን/የቀረበውን ማስረጃ ሐሰት ወይንም ደግሞ የፈጠራ ቢሆን ኖሮ ከፍ ሲል ከላይ ከነምስሉ “ይቀርታ! የፈለጉትን ገጽ በብሎጉ/በስፍራው ላይ የለም/አልተገኘም!” ባላለ ነበር። እንደው በአንፃሩ ያልሰጡትን/የሌለውን የጠይቁት እንደሆነ ይሉኝታ በሌለው ሁኔታ እንደሚከተለው ነበር የሚመልስሎት:
Your search – … – did not match any documents.
Suggestions:
• Make sure all words are spelled correctly.
• Try different keywords.
• Try more general keywords. ተግባባን? እንግዲህ አሁን በአንድ ድምጽ “የሊንኩ” ጽሑፍ የት ገባ? በማለት ጥያቄአችን ለእውቀት አላባው ጽንፈኛ ድርጅት “ለማህበረ ቅዱሳን” እናቅርብ።
ጥብቅ ማሳሰቢያ፣
“ደጀ ሰላም” የማ/ቅዱሳን ናት በሚል “ኢትዮፕያንሪቪው” ላይ ለተስተናገደ ጽሑፍ የተሰጠ ማስረጃዊ ምላሽ” የሚለውን ድረ ገጽ እንደማንኛውም የነፃ ሃሳብ ማንሸራሸሪያ አስተናገደ እንጅ የጽሑፉ ባለቤት አይደለም። መጠሪያ ስሙ በሰማችሁና ባያችሁት ቁጥር ጠበል እንደገባ ስይጣን የሚያስበረግጋችሁ፣ የሚያጮኸችሁና የሚያስደነግጣችሁ የቀድሞ “ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን?” መጽሐፍ ጸሐፊ “ደጀ-ሰላም” የማን ናት?” ሲል ለጻፈው ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ ማለትን ትታችሁ የሊማሊሞ መንገድ ምን አስኬዳችሁ? ደግሞስ ሌሎች በርካታ ጽሑፉን ያስተናገዱ ድረ ገጾችን ትታችሁ ወደ “ኢትዮፕያንሪቪው” የዘለላችሁ ምን ዓይነት መልዕክት ለማስተላለፍ ነው?
“ተሐድሶዎቹ ይኼንን ራሳቸው ስድብ ማጠናከሪያነት ተጠቀሙበት” የተጻፈው በአንድ ሰው! ጻሐፊውም ከልጅነት እስከ እውቀት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ያን ትምህርትና ስርዓተ ቤ/ያን በሚገባ ያደጉና የተፈተኑ እንዲሁም በመንፈሳዊ ህይወታቸውና በመልካም ስነ ምግባራቸው የተፈተኑ ቀደም ሲል የስነ መለኮት ሊቅና ፈላስፋ ከሆኑትና ከብጽእ አቡነ መርሃ ክርስቶት እግር ስር ትምህርተ ሃይማኖትን የቀጸለና ያጠና በመቀጠልም በሁለቱ የነገረ መልኮት ተቋሞች ማለትም በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅና አባ ሰላማ ካሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተው በሚገባ ትምህርታቸውን የተከታተሉ “ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን? የሚለውን መጽሐፍ በመጻፋቸው ለዓመታት ከለፉበት ት/ቤት ታግደው ለስደት ህይወት የተዳረጉ ወጣት ጸሐፊና መምህረ ወንጌል በዲያቆን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል ተጻፈ። ደግሞስ ከመቼ ነው ወደ ተሃድሶ ጎራ የተመደቡ? በነገራችን ላይ “ማህበረ ቅዱሳን” የሚስጨንቅ ግለሰብ ሁሉ “ተሃድሶ” ማለትም ሲያንስ ነው።
ለክፉ ላይ እንዳልተኛ አንቃኝ!
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
[email protected]
May 23, 2012

እኔን የሚገርመኝ ስለ ቢተ ክርስቲያን ጉዳይ እዚህ መተህ መቸክቸክህ ነው. ነው ወይስ ስለ ኦርቶዶክስ ሰዉ መጥፎ አመለካከት እንዲኖረው ለምታደርገው ጥረት እንዲያግዝህ ነው. ምን ብትለፉ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አትጠፋም እናንተ እንዳትጠፉ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከምትሰሩት ነገር ተመለሱ. ለሁሉም ልብ ይስጥልን እግዚአብሀር. አሚን!
አንተ የመለስ ወንድም የዚህ አለም አሳሳች እርኩስ መንፈስ ያደረብህ ስትሁን ሰሚ እስክታገን ለቅልቅ.ሃይማኖታችን በአንተ አይነቱ የቅቤ እሾክ አይሰናከልም.እውነቱ እስኪወታ እና ትግህን እስክትይዝ ለፍልፍ አምላክ ሆይ ፊርድህ በአንተ አይነቶቹ ላይ አይዘግይ አንተም እንደ አለቃህ መለስ ማንነትህ ሲጋለት ለማየት ያበቃን ዘንድ ምኖታችን ነው አትተራተር ግዘው ቅርብ ነው የቅዱሳን አምላክ ማህበረ ቅድሳንን ተብቅልን በነሱ ተጋድሎ ነው ሃይማኖታችን እስካሁን የቆየችው እንጅ እንዳንተ ያሉ ከሃዲያን ዪቺን ሃይማኖት ለማትፋት ሲታገሉ ቆይተዋል ደሞም መሃበረ ቅድሳን መቸም አይተፉም እና አትልፋ አገራችን ያለን ኦርቶዶክሶች ሁሉ እንደምንደግፋቸው እወቅ ጊዚ ሁሉን ያሳይሃልና አትቸኩል—
The so called Dn Mulugeta is suffering from inferiority complex. He needs to be treated as soon as possible. He has been suffering since he failed to get the required score to join Univesities, in Ethiopia. finally as he had no options, he joined St. Silase Theology Collage. From the collage, becuase of his misconduct and Tehadiso belief he was kicked out from the collage. Considering that nobody knows him in America, he talks a lot, maily about himself; which is typical sign of inferiority complex. Please lets do something and help him so that he can get the treatment.
The other thing, it doesn’t need to be a prophet to tell that the end of Elias Kifle, the bloger and a friend of Mulugeta would be the same as Solomon Tekalign. They are good friends to Isayas Afeworke and Meles Zenawi; the enemies of the people of Ethiopia.
I did not expect such a tone from people who seems to care more about religion and Godthan nothing.
MK seems to me an organization who got an opportunity to access the most important part of our future, youth community but also lost control of what to do with it. Hopefully, they can fix it eventually with better tone than what we have seen hereabove
Boys, an effort to adjust MK and work on minimum differences with them is the best bet for now. I do not think and believe MK is Ethiopians immediate enemy versus the Woyanes and their racist ideology.Honestly, I liked MK lately because our Fascist, PM Meles do not like them not only that this incident made me to revistit MK again .
Whatt I found out is MK is as a group like any kind of religious sect knocking adjacen(different) door to get in to the same house heaven.
Please, lets concentrate on our main task a head of us. Religious difference will never be solved unless tiny tolerance sprayed over it.
Lets hug and say Freedom Freedom Freedom Freedom together
ማህበረ ቅዱሳን የሰዎች ሃሳብ ዉጤት መስሎህ አትሳሳት:: ማህበሩ የተመሰረተው በባለበቱ ፍቃድ በደሙ የመሰረታትን ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንደ አናንተ ካሉት የመድህን አለምን ስሙን ብቻ እንጅ ተግባሩን እና ፍቃዱን ከማታውቁት የትንቢት መፈጸሚያዎች ለመጠበቅ ነው:: ያስከተልካትን “ዲ/ን” የምትል ታርጋ አይቶ የሚሳሳት ትውልድ አሁን የለም:: በዚህ ወቅት ድምጽን ወይም በተለይ ላንተ መቀባጠርን ሳይሆን ተግባርን በማይት የሚደግፍና የሚቃዋም ትውልድ ስለሆነ ያለው በከንቱ አትድከም:: ማህበሩ ገንዘቡን: ጊዘውን እና እውቀቱን ለቤተ ክርስቲያኑ የሚያውል ትዉልድ ነው ያፈራው:: አንተና መሰሎቻችሁ ታሪካችን እና ማንነታችንን ለማጥፋት በገንዘብ እና በጊዜዊ ጥቅም ተታላችሁ ስትማስኑ ታልፉአትአላችሁ አንጅ አይሳካላችሁም::
Lantena lemeselochih egziabher libona yistachihu