ማን ይሁን እውነተኛ? “ለማህበረ- ቅዱሳን” የተሰጠ ምላሽ:
የሀገሬ ሰው ቅጥፈት የለመደች እጅ ከንስሃ ይልቅ ለዓመጽ ቅርብ ነች እንዲል ይህ ነፍሰ ገዳይ ሳለ ራሱን “ማህበረ ቅዱሳን” በማለት የሚጠራ ስሙ የማይጠራ የነገሰበት የጎበዝ ስብስብ በስህተት ላይ ስህተት፣ በውሸት ላይ ውሸት፣ በአመጽ ላይ አመጽ መስራትና መደጋገም ሁነኛ መታወቂያው ለመሆኑ ማናችንም አንስተው። ይህን መሰሉ የማህበሩ (“የማህበረ ቅዱሳን”) መሰሪ ድርጊት በማጋለጥ ረገድም ጸሐፊው “ደጀ ሰላም” በመባል የሚታወቀው የሽብርና የሁከት ማእከል መካነ ድሩ “የማህበረ ቅዱሳን” ለመሆኑና ማህበሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያንና አገልጋዮችዋን ማተረማመስ እንዲሁም ማሳደድ በተቀናጀ መልኩ እየተያያዘው ሲመጣ የቀድሞ ስራዎቹ (ባለቤትነቱን የሚመሰክሩና የሚያረጋግጡ) ከስፍራው በመቀል የእኔ አይደለም በማለት እስከመካድ ደርሶል። በዚህም ሳይመለስ የሚያቀኝ የለም በሚል የሞኝ ፈሊጥም እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ ያለውንና የሌለውን አቅም በመጠቀም ከወትሮ በበለጠ ሁኔታ ሰማያዊትና ቅድስት በሆነችው ቤ/ያን ላይ ሽብርንና ሁከትን በመዝራት ረገድ እየገፋበት እንደሚገኝ በማከል ከጥቂት ቀናት በፊት የሚከተለውን ለንባብ መብቃቱ ይታወሳል።
“ይህ የሚመለከቱት መረጃ “ደጀ ሰላም” በመባል የሚታወቀውን ድረ-ገጽ/ብሎግ ሲጀመር ማኅበሩ የራሱ እንደሆነ በይፋ በድህረ ገጹ የገለጸበት/ያስተዋወቀበት በእንግሊዝኛ የድረ-ገጹ የመጀመሪያ የጽሑፉ “ሊንክ” ነበር። በተለይ deje-selam.blogspot.com/…/Ethiopia-mahberekidusan-eotc-past.html- የሚለውን ጽፈው ለመጎልጎል የሞከሩ እንደሆነ “ጭራሽ ከስፍራው ተነቅለዋል” የሚል መልስ ነው የሚያገኙ ለምን? ማኅበሩ ስራዬ ብሎ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን መዋጋትና ማፈርስ ብሎም ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንና የአባቶችን ክብር በሚነካ መልኩ ከአንድ በኢትዮጵያዊ ባህልና ወግ ያደገ ፍጡር በማይጠበቅ ልቅነትና ዋልጌነትን በእጅጉ አይለው በሚታዩበት ሁኔታ ማዋረድና ማንቋሸሽ እየተያያዛው ሲመጣ ጽሑፉን ከስፍራው በመንቀል የእኔ አይደለም እስከማለት ደርሰዋል።” ታድያ ይህን ቁልጭ ያለውን በማያሻማ አገላለጽና ግልጽ መርጃ/ሰነድ የተደገፈውን ሐቅ ሽምጥጥ አድርገው ለመካድ የሆነውና ያልሆነውን ያልተባለና ያልተጠየቁትም ለመቀባጠር እንቅልፍ አጥተው ሰንብተው ኖሯል። በዚህ አጋጣሚ “… ምላሽ” በማለት የቀረበውን የቅጥፈት ስራ ሳይውል ሳያድር በኢ-ሜይል አድራሻዬን የላክልኝ ወዳጄ መ/ም ደመላው እጅግ አድርጌ ላመሰግንህ እወዳለሁ።
ውድ አንባቢ! “ልሳነ ሌዋታን “ደጀ ሰላም” የማን ናት!” በሚል ርዕስ የቀረበውን እውነት ለማደፋን “ደጀ ሰላም” የማ/ቅዱሳን ናት በሚል “ኢትዮፕያንሪቪው” ላይ ለተስተናገደው ጽሑፍ የተሰጠ ማስረጃዊ ምላሽ” በሚል በመካነ ድሩ በኩል “አይደለም! ሐሰት ነው የተሃድሶዎች ውንጀላ ነው” ሲል ሀፍረት ሳይሰማቸው ዳግም ለማደናገር ቃጥታቸውል። ታድያ ዲ/ን ሙሉጌታ ለቃላቸው እማኝ በዋናነት በማስረጃነት ያቀረቡትን “ሊንክ” (deje-selam.blogspot.com/…/Ethiopia-mahberekidusan-eotc-past.html-) ተጭነው እውነቱ እንዲያረጋግጡ በተጠየቀው ጥያቄ መሰረት ነው ማላሹ የተሰጠ ወይስ ሃሳባቸውንና ሐተታቸውን “ደጀ ሰላም” “የማህበረ ቅዱሳን” ለመሆኑ አክለው በተጻፉ ላይ? መካነ ድሩ “የማህበረ ቅዱሳን” የሚገልጽና የሚያሳይ ማህበረ ቅዱሳን “ደጀ ሰላም” መካነ ድር የእኔ ነው ሲል ያስተዋወቀውና ራሱ ያስተዋወቀበትን በጸሐፊው ለመረጃ የቀረበውን ሊንክ የት ገባ? ለምንስ መልስ ሳይሰጥበት ተዘለለ? መካነ ድሩ “የማህበረ ቅዱሳን” ለመሆኑ በማያሻማ መልኩ የሚያሳይ ተብሎ በብቸኛነት ማስረጃ የቀረበው እኮ (deje-selam.blogspot.com/…/Ethiopia-mahberekidusan-eotc-past.html-) የሚለውን ነው? ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ይሉት እንዲህ ያለውን ነው።
እንግዲህ ጎግልም “የተሃድሶ” ነው! ካልተባለ በስተቀር ቀድሞ የሰጡትን ቢጠይቁት ያለውን የሚሰጥዎት የሚያረጋግጠው ሐቅ ይህ ነው። “ደጀ ሰላም” የምትባለውን ልሳነ ሌዋታን የግብረ እከዩ ድርጅት “የማህበረ ቅዱሳን” ለመሆንዋ የሚከተለውን “ሊንክ” ጎግል በሚባለው ገጽ ላይ አስፍረው ይጨቁኑትና እውነቱን ይለዩ። “(deje-selam.blogspot.com/…/Ethiopia-mahberekidusan-eotc-past.html-)
ጎግል የዋዛ አይደለም! የተባለውን/የቀረበውን ማስረጃ ሐሰት ወይንም ደግሞ የፈጠራ ቢሆን ኖሮ ከፍ ሲል ከላይ ከነምስሉ “ይቀርታ! የፈለጉትን ገጽ በብሎጉ/በስፍራው ላይ የለም/አልተገኘም!” ባላለ ነበር። እንደው በአንፃሩ ያልሰጡትን/የሌለውን የጠይቁት እንደሆነ ይሉኝታ በሌለው ሁኔታ እንደሚከተለው ነበር የሚመልስሎት:
Your search – … – did not match any documents.
Suggestions:
• Make sure all words are spelled correctly.
• Try different keywords.
• Try more general keywords. ተግባባን? እንግዲህ አሁን በአንድ ድምጽ “የሊንኩ” ጽሑፍ የት ገባ? በማለት ጥያቄአችን ለእውቀት አላባው ጽንፈኛ ድርጅት “ለማህበረ ቅዱሳን” እናቅርብ።
ጥብቅ ማሳሰቢያ፣
“ደጀ ሰላም” የማ/ቅዱሳን ናት በሚል “ኢትዮፕያንሪቪው” ላይ ለተስተናገደ ጽሑፍ የተሰጠ ማስረጃዊ ምላሽ” የሚለውን ድረ ገጽ እንደማንኛውም የነፃ ሃሳብ ማንሸራሸሪያ አስተናገደ እንጅ የጽሑፉ ባለቤት አይደለም። መጠሪያ ስሙ በሰማችሁና ባያችሁት ቁጥር ጠበል እንደገባ ስይጣን የሚያስበረግጋችሁ፣ የሚያጮኸችሁና የሚያስደነግጣችሁ የቀድሞ “ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን?” መጽሐፍ ጸሐፊ “ደጀ-ሰላም” የማን ናት?” ሲል ለጻፈው ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ ማለትን ትታችሁ የሊማሊሞ መንገድ ምን አስኬዳችሁ? ደግሞስ ሌሎች በርካታ ጽሑፉን ያስተናገዱ ድረ ገጾችን ትታችሁ ወደ “ኢትዮፕያንሪቪው” የዘለላችሁ ምን ዓይነት መልዕክት ለማስተላለፍ ነው?
“ተሐድሶዎቹ ይኼንን ራሳቸው ስድብ ማጠናከሪያነት ተጠቀሙበት” የተጻፈው በአንድ ሰው! ጻሐፊውም ከልጅነት እስከ እውቀት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ያን ትምህርትና ስርዓተ ቤ/ያን በሚገባ ያደጉና የተፈተኑ እንዲሁም በመንፈሳዊ ህይወታቸውና በመልካም ስነ ምግባራቸው የተፈተኑ ቀደም ሲል የስነ መለኮት ሊቅና ፈላስፋ ከሆኑትና ከብጽእ አቡነ መርሃ ክርስቶት እግር ስር ትምህርተ ሃይማኖትን የቀጸለና ያጠና በመቀጠልም በሁለቱ የነገረ መልኮት ተቋሞች ማለትም በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅና አባ ሰላማ ካሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተው በሚገባ ትምህርታቸውን የተከታተሉ “ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን? የሚለውን መጽሐፍ በመጻፋቸው ለዓመታት ከለፉበት ት/ቤት ታግደው ለስደት ህይወት የተዳረጉ ወጣት ጸሐፊና መምህረ ወንጌል በዲያቆን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል ተጻፈ። ደግሞስ ከመቼ ነው ወደ ተሃድሶ ጎራ የተመደቡ? በነገራችን ላይ “ማህበረ ቅዱሳን” የሚስጨንቅ ግለሰብ ሁሉ “ተሃድሶ” ማለትም ሲያንስ ነው።
ለክፉ ላይ እንዳልተኛ አንቃኝ!
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
[email protected]
May 23, 2012
