የአዲስ አበባ አስተዳደርና ክፍለ ከተማው የዜጎችን መብት እየተጋፉ ነው ተባለ

ዜጎች በፍርድ ቤቶች የተከበረላቸው የመብት ጥያቄ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ተፈጻሚ እንዳይሆንና ያለዋጋ እንዲቀር እያደረጉ መሆኑን፣ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም መምርያ አስታወቀ፡፡