የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሥልጠናዎች ተደጋጋሚና አሰልቺ ናቸው ተባለ
“ሥልጠና ለማሰልቸት ሳይሆን ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል ነው” የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን
የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ለሚመለከታቸው የመንግሥት መሥርያ ቤቶች ሠራተኞች እየሰጣቸው ያሉት ሥልጠናዎች ተደጋጋሚና አሰልቺ መሆናቸውን የውይይትና የሥልጠና ተካፋዮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡