የመድረክ ግንባር መሆን በገንዘብ እጥረት እየተጓተተ ነው

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ወደ ግንባር የመሸጋገር ሒደት አባላቱ የሆኑ ሁለት የደቡብ ፓርቲዎች በገጠማቸው የፋይናንስ እጥረት እየተጓተተ መሆኑ ታወቀ፡፡