ገላው ልጅ ወለደ በእንግዳ ታደሰ
ጀግና አምጣ ጀግና ወልዳ አቁማለች፣
እናት ምድር ልጅ ለመውለድ አርጣለች፣
አርባ ዓመታት አልፏት መክና ተክዛለች፣
ብለን አዝነን ቱቢት ለብሰን ባዘንበት፣
ጀግና ወጣ ! ዘራፍ ብሎ ! ከኢሳት ቤት፡፡
የኛ ! ቧዚዝ! የኛ ጀግና ! የቴዎድሮስ ልጅ፣
ጃሎ ! ብሎ በአዳራሹ አዋጅ ቢያውጅ፣
የት ይደበቅ ? የት ይሸገግ የሹምባሽ ልጅ ?
አይኑ ብልጥጥ ! ፊቱ ድንግጥ ፣
እስኪመስል ያችን ድንቢጥ ፣
አሸበረው የገላው ልጅ ያንን አይጥ፡፡
እንግዳ ታደሰ / ኦስሎ ኖርዌይ – ለጀግናው አበበ ገላው መታሰቢያ ትሁንልኝ ፡፡