በጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሳያገኙ የቆዩ 15 ሺሕ የክስ ፋይሎች ፍጻሜ ሊያገኙ ነው
– በሥራው ለሚሳተፉ ዳኞች 400 ሺሕ ብር ተመድቧል
(በብርቱካን ፈንታ)
በፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ለረዥም ጊዜ ውሳኔ ሳያገኙ የቆዩ 15 ሺሕ ውዝፍ ፋይሎች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት፣ ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ኢትዮጵያ ጋር ሐምሌ 14 ቀን 2002 ዓ.ም. አደረጉ፡፡