ክርስቲያኑ ማህበረሰብ ከሙስሊሙ ጋር እንዲተባበር ጥሪ ቀረበ
እስላሙም ወገናችን ክርስቲያኑን በመደገፍ፤ ክርስቲያኑም ወገናችን እስላሙን በመደገፍ ሁሉም እንዲነሳና ድምጹን እንዲያሰማ ጥሪየን አቀርባለሁ” ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መልከጸዲቅ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 4 ቀን 2004 ዓ.ም. May 12, 2012)፦ ህጋዊውና በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ የሆኑት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መልከጸዲቅ በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ እደረሰ ያለውን አስከፊ ጭፍጨፋ በማውገዝ መላ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጎን እንዲቆም ጥሪ አስተላለፉ።