የኢትዮጵያን ሪቪው ርዕሰ አንቀጽ
የኢትዮጵያን ሪቪው ርዕሰ አንቀጽ
ቀዳሚው ትውልድ “አፍንጫን ሲመቱት ዓይን ያለቅሳል” ይላል። ይህ ስነ-ቃል ብሃራዊ ስንቅ ሲሆን በአንድ ኣካባቢ ያለ ኢትዮጵያዊ አካል ሲነካ በሌላው በኩል ያለው ወገን ያማል! ብሎ እንዲነሳ ይነሽጣል።
ብዙሃዊት ሃገር ኢትዮጵያ በአራቱም ማእዘናት ያሉት ልጆችዋ ለጋራ ፍትህና እድገት ካልቆሙ ሁልጊዜም እንዲሁ እንዳነከሰች ትኖራለች። ባንድ ጎራ ያለው ባህላዊ ቡድን በባህሉ ወይም በሃይማኖቱ ጥቃት ሲደርስበት ዘራፍ! አፍንጫን ሲነኩት አይን ያለቅሳል ብሎ በሌላው የሃገሪቱ ክፍል ያለው ወገኑ ካልተነሳ የአንድነት ወዙ የቱ ጋር ነው? ኣንድነት ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ወገን እና ሃይማኖት እየለየ ጥቃት ሲፈጸም ሌላው ወገን ለወገን ደራሽ ወገንነቱን በተግባር ሲያሳይ አይደለምን?
ዛሬ የብዙሃዊት ኢትዮጵያ ባህላዊ ቡድኖች አንዴ በባህላዊ ቡድናቸው አንዴ በሃይማኖታቸው ጥቃት ሲደርስባቸው ይታያል። ለአብነት በጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጭፍጨፋና ማፈናቀል እንዲሁም በአማራና በአፋር ወንድሞቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃትና በእስልምና ተከታዮችና ዘንድ እየደረሰ ያለው የመንግስት ጣልቃ ገብነት እንዲሁም በገዳማትና በክርስትና ሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚፈጸመው ግፍ ይጠቀሳሉ።
እነዚህ የባህል ቡድንንና ሃይማኖትን እየለዩና እያነጣጠሩ የሚፈጸሙ ግፎች የኢትዮጵያዊያንን የአንድነት መንፈስ ሊፈትኑ የመጡ ታሪካዊ ክስተቶች ናቸው። በመሆኑም እስልምናው ሲነካ ክርስቲያኑ ፣ ክርስቲያኑ ሲነካ ሙስሊሙ፣ ጋምቤላውና አፋሩ ሲነካ ሌላው ኢትዮጵያዊ ቀፎው እንደተነካበት ንብ ብድግ ሊል ይገባዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን ግፎችን በትዕግስት በስሎ ጊዜና ሰዓት ለሚጠብቀው ታላቁ ህዝባዊ ንቅናቄ የመነሻ አደባባይ ሊያደርጋቸውና ለሃያ ዓመት የተሸከመውን ትከሻውን ያጎበጠውን ብልሹ አስተዳደር አስፈንጥሮ የሚጥልበትን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የሚያቀጣጥልበት አውድ አድርጎ ሊጠቀምባቸው ይገባል እንላለን።
ድል ለኢትዮጵያችን!!
Outstanding Editorial! God bless!!!
It is about justice, freedom and universal human dignity so, I think today we are all muslims and we are all christians, this must be the only rational answer to Melese’s and associates ocupation in today’s Ethiopia.
በጣም ጥሩ መልእክት ነው ኤልያስ
ድል ለኢትዮጵያ!
አፍንጫ ሲነካ
አፍንጫ ሲነካ ዐይን ያለቅሳል ይሉ ነበር የቀደሙት አንድነታቸውን ለመግለፅ ። የወገኑ በደል የእርሱ በደል ወገኑ ሲገፋ እርሱ እንደተገፋ አድርጎ ሲቆጠር ነበር እንዲህ የሚባል ባለፈው ዘመን። ከሰሞኑ በሰሜን አሜሪካ እንዲሁም በአንዳንድ ኢንተርኔት ገፆች እንዳየነው የክርስቲያን ወገኑን ትግል ሙስሊሙ እየደገፈ የሙስሊሙን ወገን ትግል ክርስቲያኑ እየደገፈ በጋምቤላው በአማራው በአፋሩ በኦሮሞው . . . .በሌላውም እየደረሰ ያለው ግፍና ጭቆና በአንድነት ተቃውሞውን ሲገልጽ የሚያበረታታ ነው ። የቤትሥራ ሰጥቻለው የሚለውን ወያኔን ቢያስደነግጥም። የተጀመሩት ትግሎች መቀጠል አለባቸው የሃይማኖት ነፃነት መከበር አለበት እነመለስ ዜናዊ አይደሉም ምን ማምለክ እንዳለብንና የሃይማኖት መሪዎቻችን መርጠው የሚሾሙልን በቃ በቃ ልንል ይገባል ። አምባገነናዊ አስተዳደር ማብቃት አለበት የተነጠቅናቸውን መብቶች ለማስመለስ የተጠናከረ ትግል ያስፈልገናል ። የወያኔ መንግስት ስልትና ሕግ እየቀያየረ አዳዲስ ስም እየሰየመ የሚያጸናውን በደል በቃ ልንል ይገባል።
ወያኔ ኢትዮጵያ ላይ እንደ አልቅት ተጣብቆ ደም ሲመገምግ 21 አመት አለፈው። ዘንድሮው ግን የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ላይ ተንቀሳቅሶ “እባብን በበትር መግደል እባቡንም በትሩንም ወደ ገደል” እንደሚባለው ወያኔን እንደሚያጠፋ ሳይታለም የተፈታ ነው።